ገብር ሔር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ገብር ሔር፡- ይህች ዕለት ከልዑል እግዚአብሔር የተለያያ ጸጋን(ሥጦታን) የተቀበልን ሁሉ አንደየሥራችን ምንሞገስባት አልያም የምንወቀስባት ዕለት ናት፡፡ ሁለቱም ለጥቅማችን እንጂ ለጥፋታችን አይደለም፡፡ ምስባክ፡- ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጻድቀከ በማኅበር ዐቢይ፤ መዝ ፴፱፡፰ ትርጉም፡- አምላኬ ሆይ ፈቃድህን እገልጥ(አደርግ) ዘንድ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፤ በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ፡፡ - አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ቃል ከግብር አስማምቼ እገልጣት ዘንድ ወደድሁ፡፡ እንዲህ የተዋቡ ቃላትና ሀሳቦች ሊፈልቁ የሚችሉት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ህብረት ካደረጉ ልቦች(አልባብ)ብቻ ነው፡፡ከሁሉ አስቀድሞ የጌታ እግዚአብሔር ፍቃዱ ምን እንደሆነ አውቃ ትገዛለት ዘንድ ነፍስ በትህትና ወደ ቃሉ ማዕድ መቅረብ ያስፈልጋታል፡፡ ጌታም በመጽሐፍ…
Read more...