Login
Main menu

Items filtered by date: June 2026

በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብርታትና ድካም፣ ማግኘትና ማጣት፣ስኬትና ውደቀት፣ ሰላምና ሁከት፣ ጤናና ህመም ሲፈራረቁብን ከረምን፡፡ የመጡትን በመቀበል ደስታና እንደየ ሥራቸው የተጠበቀላቸውን ለመቀበል በሞት ወደ ጌታ የሄዱትን በመሸኘት በሀዘን ስሜታችን ሲቆስልና ሲፈወስ ሲያር እና ሲታደስ ባጅተን አዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ ላደረሰን አምላካችን ሸክላ ሕይወታችን ጥላ መሆኑን ዘንግተን ዛሬም እንደ አምና አዲሱን ዓመት በአሮጌ መንፈስ ለመቀበል ለተቃረብን ሁሉ የጌታ መንፈስ ቅዱስ መልዕክት እነሆ፡፡

‹‹በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት›› ሉቃ 13፡6-9

በአንድ ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በማስተማር ላይ ሳለ ጲላጦስ በመሠዊያው ላይ በሰይፉ አርዶ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለደባለቀው ሰዎች ዘግናኝ ፍጻሜ ሊነግሩት ጀመሩ፡፡ ጌታችንም መልሶ እነዚህ ሰዎችና በሰሊሆም ግንቡ ተንዶባቸው የሞቱ ሰዎች ሁሉ ከእናንተ ይልቅ ኃጢአት የሠሩ ይመስላችኋል፤ ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ በማለት አስጠንቅቋል፡፡

ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታም ሆነ አሰቃቂ በሆኑ ሰው ሠራሽ አደጋዎች ብዙ ሰዎችን ከኋላችን ትተን ጽድቅና ኃጢአት ከሚፈራረቁበት መሬት ሥር ቀብረን እኛ ቆመናል ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ነገርግን አዚህ የመደረሳችን ምስጢር እኛ ከእነርሱ ተሽለን መገኘታችን ይሆን?

ጌታችን ለጥቆ በወይኑ እርሻ ተተክላ ሦስት ዓመት ሙሉ ፍሬ ስላልተገኘባትና እንድትቆረጥ ከተሰጠባት ትዕዛዝ በወይኑ አትክልተኛ ጸኑ ልመና ሰለዳነች በለስ ማለፊያ የሆነ ምሳሌ በመስጠት የእኛን እዚህ የመድረስ ምስጢር ገልጾልናል፡፡

የወይኑ ባለቤት በለሷ ሦስት ዓመት ባለማፍራቷ እንድትቆረጥ ትዕዛዝ የሠጠው በርሷ አለማፍራት ብቻ ሳይሆን ምድሩንም እያጎሳቀለች በመሆኗ ጭምር ነበር፡፡ የወይኑ አትክልተኛ ግን በጌታው ፊት ቀርቦ ዙሪያውን እስክኮተኩትላትና ፍግ እስካፈስላት በዚህ ዓመት ደግሞ ተዋት ወደፊት ብታፈራ ፣መልካም ነው ያለዚያ ግን ትቆርጣታለህ በማለት ከመቆረጥ አድኗታል፡፡

መተርጉማን አንድ ሰው የተባለ ጌታ እግዚአብሔር፣በለስ የተበሉ ቤተ እስራኤል፣ የወይን እርሻ የተባለች ቤተመቅደስ የታነጸባት ኢየሩሳሌም፤ ሦስት ዓመት የተባለ ዘመነ መሳፍንት፣ዘመነ ነገሥት ዘመነ ካህናት መሆኑን ያትታሉ፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ተስፋ በተሰጣቸው ሕግ በተሠራላቸው በእስራኤል ዘንድ ሃይማኖት ምግባር አገኝ እንደሁ ብሎ በብሉይ መምህራን አድሮ ቢመጣ አጣባቸው፡፡

መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤልን ለሌላው ክፉ አብነት ሆነው እንዳያስጎዱ አጥፋቸው ብሎ ቢናገርም ቅዱስ ሚካኤል ተራድቼ ምግባር እስካሠራቸው ታገሥ ብሎ በለመነው ልመና ለመትረፋቸው ምሳሌ ነው፡፡ በፋርስ፣በባቢሎን፣የገጠማቸው ስደት ጨርሶ አላጠፋቸውምና፡፡

አንደም አንድ ሰው የተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ በለስ የተባሉ አይሁድ፣ ሦስት ዓመት የተባሉ ጌታ በሥጋ ተገልጦ ያስተማረው ሦስት ዓመት ነውና ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዓይተውከክፋታቸው መመለስ መልካም ፍሬ ማፍራት ስላልቻሉ የወይኑ አትክልተኛ የተባለው መጋቤ አዲስ ቅዱስ ገብርኤልን አጥፋቸው ቢለው ምንም እንኳ በጥጦስ ቢማረኩም ፈጽሞ ከመጥፋት አማልዶ እንዳዳናቸው የሚያሳይ ነው፡፡

አንድም አንድ ሰው የተባለው ጌታ በለስ የተባልን በስሙ አምነን የተጠመቅን ክርስቲያኖች ነን፡፡ ሦስት ዓመት የተባለ የሰው የእድሜው ዘመናት ናቸው፡፡ ይኸውም ሕጻንነት፣ውርዝውናና ዕርግና ናቸው፡:፡ ጌታ በእነዚህ የእደሜ ዘመናችን ሁሉ መልካም ፍሬ አፍርተን እንገኝ ዘንድ ይጠብቅብናል፡፡ እንድም በሦስቱ ክፍላተ ጊዜያት በነግህ፣በሰርክ፣በሌሊት መልካም ሥራ ይጠበቅብናል፡፡ ባለን ጊዜ ጠባቂ መልአካችንን ነፍሳችንን ከሥጋችን እንዲለይ ‹‹ቁረጣት›› ብሎ ማዘዙን ያሳያል ጠባቂ መልአኩ ግን ጌታ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ እንዲሰጠን ‹‹ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት›› በማለት ይለምናል፡፡

ጠባቂ መልአኩ ‹‹ በዚች ዓመት ደግሞ›› ማለቱ ተመሳሳይ ልመና ብዙ ጊዜ ማቅረቡን ያመላከታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ልመና ቅዱሳንንና መላእክት ምን ያህል ጊዜ አቅርበውልን ሕይወታችንን ታደገዋት ይሆን?

በተጨማሪም የወይን ጠባቂው ካህናትን ይወክላል፡፡ የእምነት ፍሬ ያልታየባቸውን የስም ክርስቲያኖች ለሌሎቹ መጥፎ አርአያ እንዳይሆኑ ከምእመናን አንድነት ለይዋቸው በተባሉ ጊዜ እንደ መኮተኮት ፍግ እንደማፍስስ መክረን አስተምረን መልካም ሥራ እንድናሠራቸው ታገሰን በማለት በሚያቀርቡት ጸሎት በሚሠውት መሥዋዕት መማጸናቸውን ያመለክታል፡፡

ይቺን በለሰ ማወቅ ራስን ማወቅ ነውና ቀርቤ እመረምራት ዘንድ ወደደኩ፡፡

፩. የመጀመርያው በለሲቱ ፍሬ ለማፍራት የሚያስችላት ማንኛውም ነገር ተሟልቶላት ነበር፡፡ ሁኔታዋን በቅርበት የሚከታተል ጠባቂም ነበራት ነገር ግን ፍሬ አልተገኘባትም፡፡ እኛም መልካም ፍሬ እንድናፈራ የሚያስፈልጉን ሁሉ ተሟልተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ፣ቅዱሳት መጻሕፍት፣ምሳሌ የሚሆነን የቅዱሳን ሕይወት፣ካህናትና መምህራን፤ ከዚያም በላይ የቅዱሳን መላእክት እርዳታና በእኛ ውስጥ የሚሠራ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ አለ፡፡ ግን በአንዱም ተጠቅመን መንፈሳዊ ፍሬ ልናፈራ አልቻልንም፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ፍሬ የሚጠብቀው ከእርሱ የሚጠበቅበትን ከፈጸመ በኋላ ነው፡፡ ኢሳ 5፡1

፪. በለሷ ከሩቅ ሲያይዋት ልምላሜ ስለነበራት ፍሬ አይኖራትም ተብሎ አልተጠበቀም፡፡ ደረቅ ብትሆንማንም ፍሬ አይፈልግባትም ነበር፡፡ ይህ ቅጠል ወይም ልምላሜ በእኛ ሕይወት ያለ ‹‹መስሎ መታየት›› ነው፡፡ ቤተክርስቲያን በመመላለስ፣በማስቀደስ፣በሽንገላ ከንፈር፣ጉባኤ በመካፈል ወዘተ…ብቻ የተወሰነ ሕይወት ነው፡፡ ይህ የንሰሓ ፍሬን የሕይወት ለውጥን የመንፈስ መታደስን ካለመጣ በራሱ ዋጋ ሊያሰጥ አይችልም፡፡ ክርስቲያን የተባልነው ሆነን ለመገኘት ፍሬ ለማፍራት ነው፡፡ የመንፈስ(የክርስትና) ፍሬ የተባሉትም በገላትያ 5፤22 የተጠቀሱትና እነርሱን የሚመስሉ ምግባራት ናቸው፡፡

፫. የበለሷ ጌታ ከበለሷ ፍሬ ፈልጓል፡፡ አንድ ሰው ካህን ከሆነ የክህነት፣መነኩሴ ከሆነ የምንኩስና፣ሰባኪ ዘማሪ ከሆነ የአገልጋይነት፣ሰንበት ተማሪ ከሆነ የደናግላን በአጠቃላይ ክርስቲያን ከሆነ የክርስትና ፍሬ ይታይበት ዘንድ ግድ ነው፡፡ ስም ብቻ መሸከም ክብር አያሰጥም፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ መንግሥት በሌላ ሲተካ የቀድሞው መንግሥት የጦር ጀነራሎች፣ኮሎኔሎች፣ሻለቆችወዘተ…ይኖራሉ፡፡ ሁሉ በአዲስ ሲተኩ ሥልጣናቸው ይውሰድና ስም ብቻ ተሸክመው ይቀራሉ፡፡ የሚያዙት አንድ ወታደር ሳይኖር ታሪክ ብቻ እያወሩ ሕይወታቸውን ይገፋሉ፡፡ ስሙ ሥራ ካልሠራ ለመጠሪያነት መለጠፉ ነበርኩ ከማለት ውጪ ለምን ይጠቀማል?እኛም ክርስቲያን ተብለን ታላቅ ስም የተሸከመን መጠሪያ ብቻ እንዲሆነን ወይም ያለፈ ታሪክ ለመተረክ ሳይሆን ትቆርጣታልህ ሲባል እስከመቼ?


 

እንኪያስ ፍሬ እንዲገኝብን ምን እናድርግ?

፩.ሁልጊዜ የጌታ እግዘአብሔርን ቃል በማስተዋል በማንበብ ሕይወታችንን ማሳደግ ‹‹ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስይለዋል ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል››መዝ ፩÷፪-፫

፪.ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ፍጹም ሕብረት ያለው ሕይወት ለመምራት መጣር ይህም የቃሉን ትምህርትና የሕይወቱን አብነት በማየትና እርሱን ለመምሰል ራስን በማስለመድ የሚገኝ ነው፡፡ ጌታችን ሲመክረን‹‹ እውነተኛ የወይን ግንድ አኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያሰወግደዋል ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ይጠራዋል… ‹‹ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ፡፡ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም፡፡ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናነተም ቅርንጫፎች ናችሁ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፡፡ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፡ እነርሱንም ሰብሰበው ወደ እሳት ይጥሏቸዋል ያቃጥሉአቸውማል፡፡›› ክርስቲያን ተብሎ የክርስቶስ ኢየሱስ ቃሉንና ሕይወቱን የማይከተል ቢኖር የተገነጠለ የደረቀ ወደ እሳትም ለመጣል የተዘጋጀ ቅርንጫፍ ነው፡፡ ዩሐ ፩፭÷፩-፭ችሁጫፎችውምሸለቆችትናንን፣ፍርድኩሰትን

፫.ጸሎት፡- በሥርዓተ ቅዳሴ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክብር ደሙ ለዘላለም ሕይወት ሲታደል በዜማ በሚጸለየው ጸሎት ላይ ‹‹ ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ›› እንላለን፡፡ አንተን ደስ የሚያሰኝ ፍሬ ሃይማኖት እሠራ ዘንድ ኃይል መንፈሳዊ ስጠኝ በማለት በሥጋው እና በደሙ እንማጸናለን፡፡ ይህም የተወደደና የተጋባ ጸሎት ነው፡፡

ዮሐንስ መጥምቅ ለአይሁድ‹‹ እናንተ የእፉኝት ልጆች ከሚመጣውቁጣ እንድትሸሹ ማን አመላከታችሁ; አንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ…›› በማለት ከገሠጸ በኋላ አብርሃም አባትአለን የሚሉት ከንቱ ትምክህት አብርሃማዊ ሃይማኖትና የመንፈሳዊ ፍሬ ካልተገኘባቸው ሥልጣነ እግዚአብሔር ከአብረሃም ልጅነት ቆርጦ እንደሚጥላቸው አስጠንቅቋቸዋል፡፡ በእኛ እንዲሁ ነው፡፡ በስሙ ክርስቲያን ተብለናል ከእመቤታችን በጸጋ ተወልደናል የቅዱሳን ቤተሰብሆነናል ካልን በእነርሱ የታየ ሕይወት ሊታይብን ግድ ነው፡፡ ካለበዚያ አንቆረጣለን፡፡

.የበለሷ ጌታ የበለሷ ፍሬ አለማፍራት ብቻ ሳይሆን ያሳሰበው ያለ ፍሬ በመቆየቷ ምድሩን ጭምር እያጎሳቆለች በመሆኑም ነው፡፡በመጀመሪያው የክርስትና ዘመናት አህዛብ ወደ ክርስትና በእጅጉ ይስባቸው የነበረ የክርስቲያኖች ስብከት ብቻ ሳይሆን ይታይባቸው የነበረው ተወዳጅ ምግባር ነበር፡፡ ክርስቲያኖች በፍቅራቸው፣በትዕግስታቸው፣በትኅትናቸው፣በታማኝነታቸው፣ሀሰትን፣ዝሙትን፣ርኩሰትን፣ፍርድ ማጉደልን፣መማለጃ(ጉቦ)መቀበልን፣ዘፈንና፣ስካርን ጠብንና ክርክርን፣ተንኮልና አድመኝነትን፣ትዕቢትንና በሌሎች ላይ መፍረድን ወዘተ… በመጥላታቸው ይታወቁ ነበር፡፡ በሰላም ሆነ በመከራ ጊዜ በማግኘትም ሆነ በማጣት፣በሞትም ሆነ በሕይወትም ፍቅራቸው የማይቀዘቅዝ ደስታቸው የማይበረዝ ነበር፡፡ ስለዚህ ብዙዎችን በሕይወት በሚገለጥ ስብከት እስከ ሞት ለታመኑት አምላክ ማርከዋል፡፡ ዛሬ ግን እኛ ክርስቲያኖች እንደሚጠበቅብን ባለመሆናችን እንኳን ከውጭ ያሉት ተማርከው ሊገቡ ከውስጥ ያሉት እየወጡ ተቸግረናል፡፡

ፍሬ አለማፍራታችን ከራሳችን አልፎ ለሌሎችም የማሰናከያ ድንጋይ ስለሚሆን ነው‹‹ቁረጣት›› የሚል ትዕዛዝ ከልዑሉ የሚወጣው፡፡ የቅዱሳን ምልጃ የመላእክትና የካህናት ጸሎት ጌታ እግዚአብሔርን ከመዓት ወደ ምህረት ከቁጣ ወደ ትዕግሥት ባይመልሰው በዚህች ደቂቃ ይህን ጹሑፍ ለማንበብ እንኳ አንበቃም ነበር፡፡

ከእኛ ቀድመው የተጠሩ ፍሬ ተገኝቶባቸው ወይም ምድሪቱን በክፋት ሥራ አጎሳቁለው እንደተጠሩ የሚያውቅ ጠሪው ብቻ ነው፡፡ እኛ ለመፍረድ እውቀቱም ሥልጣኑም የለንም፡፡

እኛ ግን የቆየነው ከሁለቱ ባንዱ ምክንያት ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬ ተገኝብቶናል አልያም ‹‹ቁረጣት›› ተብሎ የመላእክቱና የቅዱሳን ምልጃ ታድጎናል፡፡ ግን ስለ እኛ በዚህ ዓመት ደግሞ ተዋት ወደፊት ብታፈራ ደህና ነው ያለዚያ ግን ትቆርጣታለህ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹የአህዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋም ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል›› ሲል መስክሯል ባለፈው ዓመት ግብረ አህዛብን ለመፈጸም ለመዳራት፣ለስካር ለሥጋ ምኞት፣ለዘፈን፤ሀሰት ለመናገር ወዘተ… ጊዜ፣ገንዘብ፣ኃይል፣ ቁርጠኝነት፣ሕብረት ከነበረን ለሚያግደን ምክንያትም መንገድ እንዳልሰጠን ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመፈጸም፣ራስን ለመግዛት፣በወይን ጠጅ ሳይሆን በመንፈስ ለመሞላት፤ለመንፈሳዊ ምኞት፣ለዝማሬ፣ እውነትን ለመመስከር፣ለሚሰድቡን ለመጸለይ በሌሎች ላለመፍረድ ወዘተ…ጊዜ፣ገንዘብ፣ኃይል፣ቁርጠኝነት፣ሕብረት፣ምክንያትን መሰበር በእኛ ዘንድ ሊገኝ የተገባ ነው፡፡ በዚህ ከመቆረጥ እንድናለን፤ለምንኖርባት ምድር መልካም አርአያ እንሆናለን ጊዜያችን ደርሶ ብንሄድም የሕይወትን ጽዋ እነቀበላለን ከቅዱሳን ሕብረትም እንደመራለን፡፡

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ቀሲስ ታምራት ውቤ

 

2006ዓ.ም.

Read more...

ታሪከ አበው: ይስሐቅ

Download
Name
Play
Size
Duration
download
ይስሐቅ
yeneta

44.7 MB
55:51 min
download
ይስሐቅ ክፍል ሁለት
yeneta

86.3 MB
1:02:53 min
download
ይስሐቅ ክፍል ሦስት
yeneta

89.1 MB
1:04:52 min

Read more...

የተሻለ ምርጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

    በተለያየ አህጉር አንድ ጊዜ ስለተሠጠች የቅዱሳን ሃይማኖት እየተጋደላችሁ፤ ዲያብሎስንና ሥራውን ሁሉ በእምነት ኃይል እየተቃወማችሁ የጌታችንን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም መምጣት በተስፋ ለምትጠባበቁ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

   ባለፉት ጊዜያቶች በላክሁላችሁ ጦማሮች ቅዱስ እግዚአብሔርን በመከተልና፤በቅድስና ስፍራው በቤቱ በመገኘት የምናገኘውን መልካም ነገርና፤ ምርጫችንም ምን መሆን እንዳለበት ተነጋግረናል፡፡ ለዛሬ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን ሌላ ሦስተኛ ጠቃሚ ነጥብ አናያለን፡፡

ከብዙ ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ(ቃል) ይሻለኛል መዝ118፥70

   ነብዩ ዳዊት በዚህ የመዝሙር ቃሉ ሁለት በሰው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡ (የሚወደዱ) እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አነፃጽሯል፡፡ አንዱ ጊዜያዊ ሌላው ዘላለማዊ፣ አንዱ ምድራዊ ሁለተኛው ሰማያዊ፣ ላንደኛው ከተገዛን ወደ ጥፋት የሚወስደን ሁለተኛው ግን ከጠበቅነው የሚጠብቀን ዘላለማዊ ክብርንም የምናገኝበት ነው፡፡ አስቀድመን የመጀመርያውን እንይ፡-

ብርና ወርቅ፡- በዓለማችን ስለ ብርና ወርቅ ተብሎ የሰው ልጅ የሆነውንና ያደረገውን ከመናገር ያልሆነውንና ያላደረገውን መናገር ይቀላል፡፡ የሚነገር ከተገኘ፡፡ ብዙ ሀገር ፈርሷል፤በርካታ ህዝብ ለባርነት ፈልሷል፤ለነፃነትና ለክብር ሳይሆን ለወርቅና ለብር ሲባል ብዙ ጦርነት ተካሂዷል ብዙ ንፁህ ደም ፈሷል፡፡ ከቤተመንግስት እስከ ቤተክህነት፣ ከንጉሰ እስከ ጳጳስ ፣ ከግል እስከ

 

ቡድን ተንኮል ገምዷል ሴራ ሸርቧል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ልጆች ወላጆቻቸውን፣ ባለትዳሮች የፍቅር የኑሮ አጋሮቻቸውን ከድተዋል ለሞትም ዳርገዋል፡፡ በዘመናችንም ብዙ ይደረጋል፡፡

 በአጠቃላይ የቀን ቅዥታችን የሌሊት ህልማችን ዕለት ተዕለት የምንባክነው ብርና ወርቅ ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ለብርና ለወርቅ ክብሩን ያልጣለ ማግኘት ይቸግራል፡፡ሴቶችና ወንዶች ለገንዘብ ክቡር ሰውነታቸውን ለዝሙት ሽጠዋል፡፡ እንኳን ሌላው ራሳቸው የሆኑትንና የሚፈፀምባቸውን ለመግለፅ እስኪቀፋቸው ተዋርደዋል፡፡ ህፃናት በመጫወቻ ዕድሜያቸው በሴሰኝነት ራሳቸውን በሳቱ ባለፀጋዎችና በገንዘብ ላበዱ ጨካኞች መጫወቻ ሆነዋል፡፡ ገንዘብ እንዲሞላ ሀብት እንዲሠምር ሰዎች እንደከብት ታርደው መሥዋዕት ሆነዋል፤ደማቸውም ለዲያቢሎስ ግብር ቀርቧል፡፡ የሚብሰውም ሰው በምድር በሰማይ የሚከብርበትን ከፈጣሪው ጋር አንድ የሚሆንበትን ሃይማኖቱን ሳይቀር በብርና ወርቅ ለውጧል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም "ገንዘብ በመመኘት ይረቡባችኋል" ቅዱስ ጳውሎስም "…ዳሩ ግን ባለጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ፤ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ፡፡ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤አንዳነዶችም ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ፡፡" ብለዋል፡፡ስለ ብርና ወርቅ ይህቺ ዓለም ምንያህል ርኲሰትን ተሸከመች፤ ፈጣሪስ የቱን ያህል ታገሠን፡፡ 2ጴጥ 2፥3፤1ጢሞ 6፥6-10

   ጌታም አስቀድሞ "ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል ወይም ወደአንዱ ይጠጋል፤ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም" ሲል አስጠንቅቆናል፡፡ ማቴ 6፥24

 

   እንዲህም ሆኖ ብርና ወርቅ እርካታን ሰጥቶን፣ ከደዌ ፈውሶን፣ ሰላምን አስገኝቶልን እውነተኛ ወዳጆችን አቅርቦልን፣ ይልቁንም ከሞት አድኖን ከእግዚአብሔር ቁጣም አስጥሎን አያውቅም፡፡ ይልቁንም በተቃራኒው ነው፡፡ " ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧል…ያ ቀን! የመዓት ቀን፣ የመከራና የጭንቀት ቀን ፣ የመፍረስና የመጥፋት ቀን ፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን ፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ፣ በተመሽጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና ሰዎችን አስጨንቃለሁ፤እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፤ ደማቸውም እንደ ትቢያ፤ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይፈስሳል፡፡ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀን ብራቸውንና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም…" ትን.ሶፎ 1፥14-18

   እንግዲህ ብዙ የምንሆንለትና የምናደርግበት ብርና ወርቅ ኃይሉና ጉልበቱ እዚህ ድረስ ነው፡፡ አንባቢው ያስተውል በደዌ የሚማቅቁ በሰላም እጦት የሚሳቀቁ በሞትና በእግዚአብሔር ፍርድ ሳያስቡት ድንገት የታነቁ ብዙ ባለፀጋዎች ከእኛ በፊት አልፈዋል፡፡ በጊዜው ካልነቃን በእኛም የሚደርስ ይኸው ነው፡፡ የሰው ሕይወቱ በገንዘቡ ብዛት አይደለምና፡፡ ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል፤ ስለ ነፍሱስ ምን ቤዛ ይሠጣል? ሉቃ 12፥13-21፣ማቴ 16፥26-27

በአንፃሩም በተሠጠን ገንዘብ መልካም ብንሠራበት ከእግዚአብሔር ዘንድ መልካም የሚሆንልን አይደለምን? ጌታም "… የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሏችሁ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ" ሲል መክሮናል ፈፅመው የተጠቀሙበትም ብዙዎች ናቸው፡፡


 

 

የእግዚአብሔር ሕግ(ቃል)፡- የሰው ልጅ ቅድሚያ ለያስተውለው የሚገባው ዋና ነገር ቢኖር ጌታ "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" ብሎ ያስተላለፈው ታላቅ መልእክት ነው፡፡ መብላት መጠጣትና መራባት ሕገ እንስሳ እንጂ ሕገ ሰብእ አይደለም፡፡ ሰው ከመብላት ከመጠጣትና ከመራባት ያለፈ ዓላማ ይዞ የተፈጠረ ፍጥረት ነው፡፡ ይኸውም ዓላማ የፈጣሪውን ክብር መውረስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል(ሕግ) መሠላልነት የሚደርስበት ሠገነት ነው፡፡ ለሰው የእግዚአብሔር ቃል ከሥጋና ከነፍስ ደዌ የሚፈወስበት መድኃኒት፤ከሥጋዊም ሆነ ከመንፈሳዊ የጠላት ሠራዊት የሚሸሽግበት ዐለት፣ ከርኲሰቱ የሚጠራበት፣ ከድካሙ የሚበረታበት፣ ከስብራቱ የሚጠገንበት፣ከሀዘኑ የሚፅናናበት፣ከድንቁርና ጨለማ ነፃ የሚሆንበት ብርሃን ነው፡፡ ሥጋ የሚያስፈልገውን ካጣ ከስቶ  ጠውልጎ ውበቱ ደምግባቱ ተበላሽቶ እንዲታይ ነፍስም የእግዚአብሔር ቃል ከተለያት ውበት ደም ግባቷ የሆነ ንፅህና ቅድስና ጠፍቶባት ጠውልጋ ተበላሽታ ትታያለች፡፡ የሥጋ ክሳትና ጉስቁልና በዓይነ ሥጋ እንደሚታይ የነፍስ ጉስቁልና በዓይነ ልቡና ይታያል፡፡ ሰው በዝሙት፣ በሀሰት፣ በስርቆት፣በክፋት፣ በሀሜት፣በስድብ እግዚአብሔርን ባለመፍራት ሰውንም ባለማፈር ሲመላለስ እንኳን በሕገ እግዚአብሔር ፀንተው ላሉ፣ በግብር ለሚመሰሉትም ይከፋል፡፡ በሁሉም ይነወራል፡፡ የነፍስም ጉስቁልና በዚህ ይታወቃል፡፡

ለዚህ ነው ነብዩ ዳዊት " ሕጉን በቀንና በሌሊት የሚያስብ ሰው ቅጠሉ እንደማይረግፍ ፍሬዋንም በየጊዜዋ እንደምትሠጥ በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ዛፍ ነው" ያለው፡፡ እስኪ ለጥቂት ደቂቃ ኑሮአችንን ያለ ውኃ ለማሰብ እንሞክር፡፡ ውኃን ብናጣ ምን ሊፈጠር ይችላል? ያለውኃ ምግባችንን ማብሰል እንዳንችል፤ ያለ ቃለ እግዚአብሔርም  እርሱን ወደማወቅ ብስለት ልንደርስ አንችልም፡፡ ያለውኃ የሥጋ ንፅህናን ማግኘት እንዳንችል፤ ያለ ቃለ እግዚአብሔርም የነፍስ ንፅህና አይገኝም፡፡ ያለውኃ ቤት መስራት እንዳይቻል ያለ ቃለ እግዚአብሔርም ሰማያዊ ቤት አይኖረንም፡፡ ያለውኃ በሥጋ መኖር እንዳይቻል ያለቃለ እግዚአብሔርም ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡ ሐዋርያት ለዚህ ነው ጌታችንን" ካንተ ወዴት እንሔዳለን አንተ የህይወት ቃል አለህ" ያሉት፡፡

   ነብዩ ዳዊት ለክብረ መንግስቱ የሚገበርለት ብዙ ብርና ወርቅ ቢኖርም ሕይወት እንደማይሆነው ከሞትም እንደማያድነው ሰለተገነዘበ ነው ሕግህ(ቃልህ) ይሻለኛል ያለው፡፡ ሰው በብር በወርቅ ከሚያጌጥ በእግዚአብሔር ሕግ ቢያጌጥ፤ በብር በወርቅ ከሚከብር በእግዚአብሔር ቃል ቢከብር ለሰውም ለእግዚአብሔርም ደስ ያሰኛል፡፡ ብዙ የምድር ባለፀጋዎች አልፈዋል ከነስም አጠራራቸውም ተረስተዋል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል የከበሩ ግን በምድርም ሆነ በሰማያት የዘላለም መታሰቢያ ቆሞላቸዋል፡፡

-ዳዊት እንደልቤ የተባለ ስለሀብቱ ብዛት ሳይሆን እግዚአብሔርን ሰለመፍራቱና ቃሉን ስለማፍቀሩ ነው፡፡                                       -ነቢያትና ሐዋርያት ጻድቃንና ሰማዕታት የሚታወሱት በባለሟልነትም የሚታሰቡት ሕጉን ሰለጠበቁና ቃሉን ሰላገለገሉ እንጂ ስለ ብርና ወርቃቸው ብዛት አይደለም፡፡ ኢሳ 56፥1-ፍፃሜ

-ሙሴም ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት እስኪነጋገር ድረስ በባለሟልነት የከበረ የግብፅን ገንዘብና ሹመት ስለመናቁ አይደለምን? ዕብ11፥23-28

   በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አብራችሁኝ የተስፋው ቃል ተካፋዮች የሆናችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ቃሉ በእኛ ቢኖር እኛም በቃሉ እንኖራለን፡፡ በትዕዛዙ የምንሔድ በቃሉም የምንኖር ከሆነ ራሱን ይገልጥልናል ይወደናልም በእኛ ዘንድም መኖርያውን ያደርጋል፡፡ ዮሐ14፥18-24

ቃሉን የማይናፍቅ ሕጉን ሲሰማ የሚሰለቸው ራሱ በፈጠረው በሚመቸው ህግ ለሚኖር ለዚያ ሰው ወዮለት፡፡ ታላቅ ፍርድ ይጠብቀዋልና፡፡ ሞት በሙስና አይታማም፡፡መማለጃም ሰጥቶትም ህይወቱን ያረዘመ ሰው ዓለም ከተፈጠረ አልሰማንም፡፡ የልዑሉን ትዕዛዝ ፍርዱንም የሚያስፈፅመው መላዕክትም በብርና በወርቅ አይደለሉም፡፡ በሲዖልም በሀብታችን የተሻለ ቦታን ልንመርጥ አይቻለንም፡፡ ያ ዓለም ብርና ወርቅ የሚሠለጥንበት ዓለም አይደለምና፡፡

ቃሉን የሚያፈቅሩ ሕጉንም የሚወዱ ግን ዝማሬያቸው ይህ ነው፡፡

ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል አቤቱ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው፡፡ ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፈጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው፡፡ መዝ 118፥1-ፍፃሜ

ስለዚህ ቃሉን የያዙ በሕጉም የሚኖሩ ግን በድል ይወጣሉ፡፡ የሲዖል ግርማም በእነርሱ ላይ ኃይል የለውም፡፡ በጽዮን ተራራ ከበጉ ጋር መኖር ዕድል ፈንታቸው ነው፡፡ እርሱ አምላካቸው እነርሱ ሕዝቦቹ ይሆናሉ፡፡ ረሃብና ጥም ፣ ደዌም ፣ጉስቁልናም፣ መገፋትና መበደልም ያቀን ሀሩርና የሌሊት ቁር አያስጨንቃቸውም፡፡ ያለፈውን ሥርዓት አሳልፎ እንደ ተስፋ ቃሉ ሁሉን አዲስ ያደርጋልና፡፡ እንደ ተስፋ ቃሉ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር መጠበቅ ወይም ለኃላፊ ብርና ወርቅ መተናነቅ ምርጫው የራሳችን ነው፡፡ የተሻለውን ለመምረጥ ህሊና ተሰጥቶናልና፡፡ ራዕይ 7፥13-17፣ 2ጴጥ 3፥13

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

 

ቀሲስ ታምራት ውቤ

Read more...

...በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ብፁዕ ነው፡፡ መዝ ፩፡፩

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

      በክፉዎች ምክር ያልሄደ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ብፁዕ ነው፡፡ መዝ ፩፡፩

በመዝሙረ ዳዊት የተመሰገኑ ጠባይዓትንና አካሄዶችን አመለካከቶችንና ተግባራትን “ብፁዕ” በሚል የውዳሴ ቃል እያጀበ ተቀኝቶ እናገኛለን፡፡

ብፁዕ የሚለው ቃል “በፅዐ” ከሚለው የግዕዝ ግሥ የሚወጣ ሲሆን የተደነቀ የተመሰገነ ንዑድ ክቡር የሚለውን ትርጉም ይይዛል፡፡

ከላይ በተቀመጠው ጥቅስ ክቡር ዳዊት ሦስት አንድን ሰው ወደ ጥፋት የሚወስዱ ጉዳዩችን አንስቶ ከእነርሱ በተቃራኒ የሚገኝ ቢኖር ንዑድ ክቡር ነው ይለናል፡፡

ቀዳሚው በክፉዎች ምክር ያልሄደ ብፁዕ(ምስጉን) ነው ይላል፡፡ ምክር አንድን ሰው ክፉውን ጠባይዕ እንዲተው መልካሙን ደግሞ እንዲያፀና አስነዋሪ ተግባር የበጀ መስሎት የሚኖር ካለ እንዲመለስ፤ የተወደደ ሥራ ለመሥራት መንገድ የጠፋውንም ለማመላከት የሚለገስ የፍቅር የበጎነት መግለጫ ነው፡፡ ሰው የሚመክረው የሚያፈቅረውንና የሚጠነቀቅለትን ነውና፡፡

የገንዘብ ልግስና ራቁት ይሸፍን ረሃብ ያስታግስ ይሆን እነጂ ከክፉ ጠባይ ሊመልስ አይችልም፡፡ ቀና መንገድም አያመለክትም ገንዘብ፡፡ ጊዜያዊ ምክር ግን ቀዋሚ ስጦታ ነው፡፡

በተቃራኒው ክፉ ምክር ደግሞ ሰውን በነፍስ በሥጋ በአሁኑም ሆነ በዘላለማዊው ዓለም ሊያጠፋው ይችላል፡፡የክፉ ምክር መዝገቡ ክፉ ልብ ነው፡፡ ጌታም በወንጌል ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ሊያፈራ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ሊያፈራ እንደማይችል አስተምሯል፡፡ ጨምሮም ሰውን የሚያረክሱ ክፉ አሳቦች ሁሉ መዝገባቸው ክፉ ልብ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል ማቴ 7፤ ማቴ 15፡፡ በመሆኑም ምክር ሁሉ እንደ መካሪው ማንነት ይወሰናል፡፡ በሕይወት ጉዞ ሰው ክፉም መልካም መካሪ ሊገጥመው ቢችልም በዚያ ተምስርቶ በሚሠራው ሥራ ወይም በሚገልጠው ጠባይ የሚወደሰውም ሆነ የሚነወረው ፤የሚሸለመውም ሆነ የሚቀጣው ራሱ ነው፡፡

ንጉስ ዳዊት በቃሉ ክፉ መካሮች እነዳሉ ከገለጠ በኋላ ብፁዕ የሚባለው ግን በነዚያ ምክር ፈቅዶም ሆነ ተታሎ ያልሄደ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ታሪክ በክፉ ምክር የተጎዱ የብዙ ሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ በዋቢነት ዘግቦ ይዟል፡፡

. የእናታችን ሔዋን በምክረ ከይሲ መመራት በራሷም ሆነ በዘሯ በመከራ ለመጎብኘታቸውና በሞት ለመዳኘታቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ መካሪ ምክሩን የሚጀምረው ጉዳያችንን /ምሥጢራችንን/ ከመስማት ነውና በመጀመሪያ ለማን ምን መንገር እንዳለብን ማስተዋል ይገባል፡፡ ምንም እንኳ የሔዋንና የአዳም በደል/ኃጢአት/ ባህርያዊ ያይደለ በክፉ ምክር ተታለው የፈፀሙት ቢሆንም ከመቀጣት አልዳኑም፡፡ ወደ ቀደመ ክብራቸው የተመለሱ በልጅ ሞት ተክሰው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ስለ ወላጅ በደል የልጅ ሞት ምን ያህል ይከብድ፡፡ ዛሬም እንዲሁ ነው በወላጆች ጥፋት ልጆች በቀደምት በደል ደኅርት መቀጣታቸው፡፡

ሔዋን እንደ ርዕስ ተነስቶ ምክርና ማስጠንቀቂያ ባልተሠጠበት ጉዳይ ላይ ቢሆን ኖሮ የሳተች ባልፈረድንባት ነበር፡፡ ነገር ግን መልካምነቱን የምታውቀው የአባትነት ድምፁን የለመደችው በእጁ ከመፍጠር አንስቶ ሁሉ እድትገዛ የሠጣት ጌታ እግዚአብሔር የመከራትን ምክር ማንነቱን በማታውቀው ለእርሷ ሕይወት ምንም አስተፅኦ ባልነበረው ባዕድ (እንግዳ) በአንዲት ቅፅበት ንግግር የብዙ ዓመቱን የፍቅር ግንኙነት ማቃለሏ ጭምር በብዙ ያስወቅሷታል፡፡

በመሆኑም ሲጀምር መካሪም ማን መሆኑን ሲቀጥልም ምክሩ በጉዳዩ ላይ አስቀድመን ከሰማናቸው አስተያየቶችም ሆነ ማስጠንቀቂያዎች ጋር ያለውም ተዛምዶ ወይም ተቃርኖ ፈትነን መጓዝ ከኛ የሚጠበቅ ዓይነተኛ ተግባር ነው፡፡ ሰው የሚያስበው የሚናገረው የሚወስነው የሚሰራው ወዘተ ለራሱ ብቻ አይደለም ውጤቱም በራሱ ብቻ አይቆምም፡፡ ላለፈ ትውልድ ታሪክ ለሚመጣውም ደኅንነት ትልቅ ኃላፊነት ተሸክሟል፡፡ የኛ ሕይወት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የብዙዎች ትክክለኛ ወይም የተሳሳተ አስተሳሰብ ምክር እንዲሁም ተግባር ውጤት ነው፡፡ የኛም ተጽእኖ በሌሎች ላይ እንዲሁ ነው፡፡ በእኛ የአካልም ሆነ የመንፈስ አብራክና ማህፀን ውስጥ ብዙ ልጆች ሳይሆን ትውልዶች አሉ፡፡ ዛሬ በክፉ ምክር ስተን የምንፈፅመው ተግባር በርካታ ትውልድን ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በመልካም ምክር ተመስርተን የምንሰራው ሥራም ለትውልደ ትውልድ ጥቅም ይውላል፡፡ ብዙዎቹም ይታነፁበታል፡፡ ስለነቢዩ ዳዊት ልጆችም እንዲህ ተጻፈ፡፡

ለ. የንጉስ ዳዊት የበኩር ልጅ አምኖን በአባቱ በኩል እህቱ የሆነችውን ትዕማርን በማፍቀሩ ምክንያት ትካዜ በዛበት፡፡ እህል የማይበላ ከመሰሎቹም ጋር የማይጫወት ስሜቱን እያሰታመመ የሚቆዝም ሆነ፡፡ ይህን የተመለከተ ኢዮናዳብ የተባለ ጓደኛውም የንጉሱ ልጅ በምን ምክንያት ደስታ እንደራቀው በጠየቀው ጊዜ በውስጡ ያለውን እረፍት የነሳውን ስሜቱን ተረከለት፡፡ የኢዩናዳብ ምክርም “ታምሜያለሁ ብለህ ተኛ ንጉሱ ልጆቹን ይወዳልና ሊያይህ ይመጣል በዛን ጊዜ ትዕማር ከእጇ እንድበላ ወደኔ ትመጣ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ብለህ ጠይቀው በዛን ጊዜ የወደድከውን ትፈፅማለህ” የሚል ነበር፡፡ አምኖን እንደተመከረው አደረገ ትዕማርም ባባቷ በንጉስ ዳዊት ወንደምሽ ታሟልና ተንከባከቢው የሚል መልእክት ደረሳት፡፡ ትዕማር የሚበላው ልታቀርብለት ወደ እልፍኙ ስትገባ ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንደ ግድ አላት ትዕማር “ወንድሜ ሆይ አይሆንም እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባም እና አታሳፍረኝ ይህን ነውረኛ ሥራ አታድርግ እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከምናምቴዎች እንዳንዱ ትሆናለህ፡፡ እንግዲህስ ለንጉሱ ንገረው እኔንም አይነሳህም ” 2ሳሙ 13፡1-ፍፃሜ በማለት የመከረችውን አልሰማትም፡፡ ከክብር አሳነሳት የንጉስ ዳዊትን፣ የራሱን፣ የትዕማርና ባጠቃላይ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ኃፍረት የሆነ ነውርን ፈፀመ፡፡ በዚህ ሳያበቃ ወትሮም ዝሙት በፍቅር ለምድ ተጀቡና ቀርባው ነበርና ሲያልፍለት ከቀደመው የከፋ በደል ፈጸመ፡፡ መጽሐፍ አምኖን ትዕማርን “ቀድሞ ከወደዳት ውድ ይልቅ ኋላ የጠላት ጥል በለጠ” እንዲል በጉልበት ካስነወራት ከክብርም ካሳነሳት በኋላ በታላቅ ውርደት ከቤቱ አስወጥቶ አባረራት፡፡

ክርስቲያኖች የዝሙት መልኳ እነሆ ይህን ይመስላል፡፡ ፊት ታጣድፋለች መብልና እንቅልፍ በመንሳት እረፍት አሳጥጣ ታስጨንቃለች፡፡ ኅሊናችን በትክክል እንዳያስብ በስሜት ግርዶሽ ታጨልመዋለች፡፡ በዚህ ላይ ለዝሙት የሚያበረታታ የሚፋፋ ክፉ መካሪ ሲያጋጥም መጨረሻዋ መራር ይሆናል፡፡

በዝሙት በተወጠረ ኅሊና ዘንድ ፍቅር አትታወቅም፣ትዕግስትም ሥፍራ የላትም፣ራስን መግዛት ምውት ናት፡፡ በመተቃቀፍ ውስጥ ፍቅር የለችም ጊዜያዊ ስሜት እንጂ፡፡ አንዱን የእንዱን አካል ማክበር አይታሰብም ተራ መጠቀሚያ አድርጎ ከመቁጠር በቀር፡፡

እህቶች ሆይ በክፉ ኅሊና ከሚያደባ በልዝብ ምላስ ከሚሸነግል በመጎምዥት ዓይን ከሚያይ ተጠንቀቁ፡፡ በማን እልፍኝ እንደተገኛችኁም አስተውሉ፡፡

ትዕማር በንፅህና ሙሽራዋን የምትጠብቅ የክርስቲያን ነፍስ ትወክላለች፡፡ ድንግልና በሥጋ ላለ ንጽህና ማሳያ ነውና፡፡ አምኖን የዓለም ምሳሌ ነው፡፡ ይህች ዓለም እኛን በሥጋ ፍቃድ አጥምዳ በኃጢአት እስክትጥለን ድረስ ዕረፍት የላትም ክብራችንን ከጣልን በኋላ ግን ትከፋብናለች፡፡ ኢዩናዳብ የዲያብሎስ ምሳሌ ነው የዚህ ሁሉ ሴራ አቀናባሪ ነውና፡፡ በዓለም ከሚሠራው ኃጢአት፣ተንኰል፣ክፋት፣ዝሙት፣ጥላቻ መከዳዳት ወዘተ…ጀርባ ያለው ክፉው የዲያብሎስ ምክር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡

ብዙዎች ወደ ዓለም እልፍኝ በክብር ገብተው በውርደት፤በሳቅ ገብተው በለቅሶ፤በዕልልታ ገብተው በዋይታ፤በሙላት ገብተው በጉድለት ወጥተዋል፡፡ አምኖን “እኅቴ” እያለ ይነጋገራት እንዳልነበር ፈቃዱን ከፈጸመ በኋላ “ይህቺን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት” በማለት ጭካኔውን ገልጿል፡፡ ዲያብሎስ ማንንም በክቡር ማማ ላይ ሲያወጣ በመልካም ሲያነጋግር ለእኔ ካለው ፍቅር የተነሳ ነው ብሎ ካሰበ የመጨረሻው የሞኝነት እርከን ላይ መቆሙን ይወቅ፡፡ ከዝንብ ማር እንደማይገኝ ከዲያብሎስም ርኅራኄን አትጠብቅ፡፡እርሱ ፍቅርን ማወቅም መፈጸምም የሚሻ ፍጥረት አይደለም፡፡

ትዕማርም የንጉስ ልጆች ደናግላኑ የሚለብሱትን ብዙ ኅብር ያለውን ልብሷን ቀዳ በራሷ ላይ አመድ ነስንሳ እጅዋንም ራሷ ላይ ጭና እያለቀሰች ሄደች፡፡

በብዙ ኅብር ያጌጠ ልብስ የተባለ በብዙ ሀብታት(ጸጋዎች) የከበረ በንጉስ ልጅ ማዕረግ የተደነቀ ተፈጥሯችንን ያመለክታል፡፡ በክፉ ምክር ግን ይህ ሁሉ ይጠፋል፡፡

ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት መበለት ሆና ተቀመጠች አምኖንም ከሁለት ዓመት በኋላ በአበሴሎም የቂም ሰይፍ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡

. አምኖን በእህቱ ላይ በሠራው በደል የተበቀለው አቤሴሎም በተራው እስራኤል በተሰበሰቡት በፀሐይ ፊት አባቱ ንጉስ ዳዊትን ለማዋረድ ከአባቱ ቁባቶች ጋር ተኛ፡፡ ይህን ታላቅ ኃጢአት ያለ ኃፍረት ይፈጸም ዘንድ ያነሳሳው ክፉ መካሪው አኪጦፌል ነበር፡፡ እርሱም በተራው ክፉ አሟሟት መጨረሻው ሆነ፡፡

እኒህ ሁሉ ታሪኮች የሚያሳዩን በክፉዎች ምክር መሄድ ለገሚሱ የሕይወት ምሬት ለተከታዩም መራር ፍጻሜ እንደሚያስተከትል ነው፡፡

ክቡር ዳዊት ንጉሱ ሳኦል ነፍሱን ሲሻ ካንዴም ሁለቴ ለመግደል የሚያሰችለው አጋጣሚ ቢመቻችለትና ዙራውያውን ያሉ መካሪዎችም እጁን እንዲያነሳ ቢጎተጉቱትም “እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄንን አላነሳም እንደ ቅንነቴ ይመልስልኛል” በማለት ክፉ ምክራቸውን አልተቀበለም በዚህም “እንደ ልቤ” እስከ መባል በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝቷል፡፡

ማጠቃለያ፡- ምክር ሰምቶ ለሚፈጽማት መልካም መሆኗ አሌ የማይባል ሀቅ ቢሆንም የምክሩን ዓይነት ግን ከእነዚህ ሕግጋት ጋር የማይጣረስ መሆኑን ማስተዋል ያሰፈልጋል፡፡

፩. የተፈጥሮ ሕግ፡- የተደነቀው ተፈጥሯችን ያለ ሕግ አልተሠራም፡፡ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ፍጡራን ጋር በኅብረት እንዲኖር የሚያደርገው የመደጋገፍና የድኅንነት ሕገጋት አሉ፡፡ በአጠቃለይ በግላዊ ተፈጥሯችን ላይም ሆነ ከሌሎች ጋር በሚያስተሳስረን የተፈጥሮ ቀመር ጋር የሚጋጭ ምክርና ተግባር በዚህ ምድር ያለንን ቆይታ ያዛባዋል፡፡ ተፈጥሮን በሠራት ዘንድን ያስጠይቀናል፡፡ ዛሬ በሥልጣኔ ወይም በነጻነት ስም ከተፈጥሮ ባህርይ ውጪ የሚፈጸሙ ብዙ አስነዋሪ ተግባራት እንደ መልካም የመብት ጥያቄ በየመድረኩ ሲነሱና የወራዙትን ሕሊና በሚማርክ መልኩ ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ዘመናዊው ሚዲያ የማኅበረሱቡን የሥነ-ምግባር ዕሴቶች ጠብቆ የማቆየትና ለትውልድ የማስተላለፍ ሚናውን ዘንግቶ ንግድ ላይ ያተኮረ በመሆኑም ለወጣቶቹ ሕይወት ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ተቀርጿል፡፡ ዛሬ ዋጋ እያሰከፈለን ያለው የዚህ ሁል ድምር ውጤት ነው፡፡

፪. የማኅበረሰብ ሕግ፡- ማንኘውም ሰው ማንነቱ ተቀርፆ የሚመጣው በዚህ እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ የመጠበቅና ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ከማኅበረሰብ መገለል ወይም አንደ ሥርዓት አልባ መቆጠር ከዚህ በተቃራኒው ከመሆን  የሚመጣ ነው፡፡

. አምላካዊ ሕግ፡ የተፈጥሮም ሆነ የማኅበረስብ  ሕግ ወይም ሌላ ሕገጋት መነሻቸው አምላካዊ ሕግ ነው፡፡ እንደ ክርስቲያን የምንሰማው ምክር ሁሉ የሚመዘነው ከዚህ አንፀር ነው፡፡ ከአምላካዊው ሕግ በተቃራኒ የሚቀርብ ምንጩ ከክፉ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የአምላክ ሕግ የአምላክ ምክር ለሁሉ እርምጃችን ሚዛን ነው፡፡

ሰው ይህንን ሁሉ በማስተዋል በክፉዎች ምክር ከመጓዝ ቢቆጠብ በሥጋውም ሆነ በነፍሱ ደኅንነቱ በዙሪያው ላሉ መሰሎቹና በተፈጥሮ ለሚዛመዱት ሁሉ የደስታና የሰላም ምንጭ ይሆናል፡፡ ትናንትን በፀፀት ዛሬን በኃፍረትና በንዴት ነገንም በፍርሃት የሚያስተናግድ ሕይወትም አይኖረውም፡፡ ስኬታማ ሕይወት ይሏል ይህ ነው፡፡

ይቆየን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ቀሲስ ታምራት ውቤ

 

ሕዳር ፳፻፮ ዓ.ም

Read more...

የነሐሴ ወር ልምምድ

ተመስጦ 
በጸሎት ጊዜ፣መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ቅዱሳት ምጻሕፍት ስናነብ፣በዝማሬ ጊዜ፣በማድነቅ ጊዜ በተመስጦ በመሆን ተመስጦን መለማመድ 
Read more...

ትውልዱ ከእመቤታችን ምን ይማራል?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

ትውልዱ ከእመቤታችን ምን ይማራል?

መግቢያ

‹‹ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ›› በማለት አባ ሕርያቆስ በእመቤታችን ስም(ለእመቤታችን) በደረሰው ቁርባን ምስጋናው ስለ እመቤታችን ንጽሕናና ቅድስና፤ አካላዊቃልን በሥጋ  በመንፈስ ቅዱስ ግብር ለመውለድ መብቃት እንደቻለች፤ የአበው ተስፋ የነቢያትም ትንቢትና ምሳሌ በእርሱዋ እንዴት እንደተፈጸመ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯል፡፡ ሊፈጽመውግን አልቻለም፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹ጐሥዐ ልብየ… ልቤ በጎ ነገርን አፈለቀ እኔ የንጉሥን ሥራ እናገራለሁ››፤ ብሎ ቅድመ ዓለም ያለ ፍጡራን አምላክ፣ ያለ ተገዢ ጌታ፣ ያለ ሎላልት ንጉሥ የሆነ፤ ድህረ ዓለም በማኅፀነ ማርያም በተዋህዶ ኋላም በመስቀል የነገሠ የእግዚአብሔርን ሥራ እናገራለሁ ብሎ ቢጀምር ሊፈጽመው እንዳልቻለ የአባ ሕርያቆስም እንዲሁ ነው፡፡መዝ 44፥1

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ(ስለ እግዚአብሔር አንድነትና ልዩ ሦስትነት) በቅጥነተ ኅሊና ሊመረምሩ የወደዱ ብዙ ሊቃውንት፤ስለ አካላዊ ቃል በተለየ አካሉ ፍጹም ሰው መሆን የማይወሰነው መወሰኑ ርቀትን ከግዘፍ፣ኃይልን ከድካም፣ባዕልነትን ከንድየት፣ሕያውነትን ከመዋቲት ፍጹም በሆነ ተዋሕዶ ሳይቀላቀሉ ሳይለያዩ ሳይጠፋፉ አንድ ማድረግ፤ ጉምቱ ጉምቱ መንፈሳውያን ሊቃውንት ጠንቅቀው ሊጽፉ የሞከሩ ቢሆንም አንዳቸውም ግን ይህን ማድረግ ሳይቻላቸው ድካማቸው ስዒን በወለደው አንክሮ ተደምድሟል፡፡

የጌታ እግዚብሔር ባሕርይ የመድኃኒታችንንም ሰው የመሆን ምሥጢር ጠንቅቆ ፈፅሞ መናገር እንዳይቻል፤ የአብ ሙሽራ የወልድ ማደሪያ የመንፈስ ቅዱስ ንጽሕት አዳራሽ ስለሆነች ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በእርሷ ስለተደረገ ነገርና ስለ ክብሯ ጠንቅቆ ፈጽሞ መናገር አይቻልም፡፡

‹‹ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር›› እንዳለ ነብዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተከበረ(ድንቅ) ነገር ይባላል ሲል ነው፡፡ቃሉ ቃለ አንክሮ ነው፡፡‹‹ድንቅ›› የሚለው ቃ አንክሮ ከአእምሮአችን በላይ ለሆነ የተከተተ መግለጫ ልንሰጠው ለማንችለው ጉዳይ የምንጠቀምበት ነው፡፡እመቤታችን ብሥራተ መልአኩን ከተቀበለች በኋላ ‹‹እስመ ገብረ ሊተ ኃይለ ዐቢያተ››አብ ቢሉ በልጁ ወልድ ቢሉ በሥልጣኑ ምድራዊ ባይደ ሰማያዊ፤ ተፈጥሯዊ ባይደለ አምላካዊ፤ ጊዜያዊ ያይደለ ዘላለማዊ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓል ብላ መስክራለች፡፡መዝ 86፥3 ፤ሉቃ 1፥49

          እንዚራ መንፈስ ቅዱስ የተባለ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ስለ እመቤታችን በጻፈው ድርሰቱ በብዙ ሕብረ አምሳል እየመሰለ ሲያወድሳት ቢቆይም የእርሷን ክብርና ገናናነት ተናግሮ መፈጸም እንደማይቻል ከተረዳው በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ሰውነቱ‹‹ኑ ዘይክል ነቢ ዕበየኪ ወአልቦ ዘይመስል ኪያኪ›› ትርጉም ‹‹ክብርሽን ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማነው? አንቺን የሚመስልሽ የለምና››ሲል መልካም ነገርን አፍልቋል፡፡

          የምሥጋና አባቱ(መምህሩ)ነዩ ዳዊት ስለ ጌታ እግዚአብሔር‹‹መኑ ይመስለከ እም አማልክት እግዚኦ›› ‹‹አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስልህ ማነው?›› ብሎ የልዑሉን ገናናነት እንደተናገረ፤ ከአማልክት የሚተካከለው ያይደለ የሚቀርበው፤የሚቀርበው ያይደለ የሚመስለው የሌለ የልዑሉ ዙፋን፤እርሱን በማኅፀኗ ተሸክማ በሥጋ ወልዳ ዓለማትን በረቂቅ በግዘ የሚመግበው ጡቶቿን አጥብታ ያሳደገች የእርሷም ክብር ገናንነት መናገር አይቻልም ሲል በምሥጢር መስሎታል፡፡ውዳሴ ማርያም ዘዓርብ

ጨምሮም ‹‹ዕበያ ለድንግል ኢይትከሀል ለተነግሮ እስመ እግዚእ ረያ›› የድንግል ክብሯ ጠንቅቆ ይነገር ዘንድ አይቻልም ጌታ መርጧታልና፡፡አብ ቢሉ ለልጁ ማደርያ እንድትሆን ወልድ ቢሉ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ከእርሷ ሰው ይሆን ዘንድ መርጧታልና፡ መምረጡንም ቅድመ ሥጋዌ ቢሉ በነቢያት ትንቢት፤ ጊዜ ጋዌ ሉ በመልክ ብራት፤ ድኅረ ሥጋዌ ቢሉ ሥጋን ነስቶ በመታየት፣ በሐዋርያት ትምህርት፣ በሊቃውንት መጻሕፍት አስረድቶናል፡፡ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ምዕመናን፤ እንዲሁም በእምነት በቀኖና የሚመስሏቸው ሌሎች የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን ዳዊት በመዝሙሩ‹‹ወዘሕጎ ያነብብ መዐልተ ወሌሊተ ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ፤እንተ ትብ ፍሬሃ በበጊዜሃ ወቈፅላኒ ኢይትነገፍ›› እንዳለ የነያትን ትንቢት፣የሐዋርያትን ትምህርት፣ የሊቃውንትን የትርጓሜ ድርሳናት፣ ከንፁሕ ምንጭ ስለ አምላካቸው ታላቅነት፤ ስለ እመቤታችንም ንፅሕና ቅስና ክ አማላጅነት ሲጠጡ በመኖራቸው ልምላሜ ነፍስ ሳይለያቸው ሥራ ሊሠሩ በተሰጣቸው ጊዜ የንስሐ ፍሬ የመንፈስ ፍሬ በማፍራት በትሩፋት ላይ ትሩፋት እየጨመሩ የእርሷን ጸጋ ክንፈ ረድዔት በማድረግ እንደ ንስር በመንፈሳዊ ሕይወትና እውቀት ሲመጥቁ ይታያሉ፡፡መዝ 1፥2-3

ክርስቲያን ለመባልና የልጅነትን ክብር ለማግኘት የቻልነው አካላዊ ቃል ከእመቤታን ተ  የቤዛነትን ሥራ በመፈጸም ዓለምን ካዳነ በኋላ ነው፡፡‹‹በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው›› እንዲል፡፡ ወረደ ተወለደ መከራን ተቀበለ ተሰቀለ ሞተ ተነዐረገ ዳግመኛ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ይመጣል ብሎ ሥጋን ተዋሕዶ በፈፀመው ሥራና ስመ ሥጋዌውን ስመ ሥርየት ስመ ድኅነት ነው በማለት ማመን ነው፡፡ይህ ሁሉ የተፈፀመ ከእርሷ በነሳው ሥጋ ነው ብሎ የሚያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያለውን የእመቤታችንን ሱታፌ መገንዘብ አይሳነውም፡፡


 

          በኦሪት ጽላት ያደረበት(የተቀመጠበት)ታቦት በሚታይ ገንዘብ የእስራኤል ዘሥጋ የአምልኮታቸው ማዕከል ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ቃሉን የሚያሰማቸው በታቦቱ ላይ በመገለፅ ነበር፡፡ እስራኤል ታቦቱን ይዘው ባህር ተከፍሎላቸው ቅጥር ፈርሶላቸው ጠላት ጠፍቶላቸው ምደረ ስት ከነዓንን ወርሰዋል፡፡ታቦት የእመቤታችን ጽላት የጌታ ምሳሌ መሆኑ በብዙ መተርጉማን የተብራራ ነው፡፡ የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነትና የእመቤታችንን ምልጃ ማዕከል አድርጋ አምልኮዋን ትፈጽማለች፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችንን መወለድ በልባቸው ይዘው ያመኑ፤ በአፋቸውም የእርሱን አምላክነት የእርሷን ወላዲተ አምላክነት የሰከሩ ምዕመናን በጥምቀት በሚገኝ ልጅነት ጥቅመ ኃጢአት ፈርሶላቸው ዲያብሎስን ድል ነስተው ርስ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረሳቸው ምሳሌ ነበር፡፡

ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያምን አልቦ (ያገለለ) ክርስትና የለም፡፡በዚህ የተቃኘ ትምህርትም ከአባቶቻችን ከሐዋርያትና ከሊቃውንት የተገኘም አይደለም፡፡ ወንጌላውያኑም እመቤታችን በወንጌል በነገረ ድኅነት የነበራትን ሱታፌ በግልጽ ጽፈውታል፤ከጽን እስከ በዓለ ጵራቅሊጦስ፡፡ ጌታችን ካረገ በኋላ እንኳ ሐዋርያት እርሷን  እንደ ታቦት በመካከላቸው አድርገው ይጸልዩ ነበረ ፡፡ጸሐፊው‹‹የኢየሱስም እናት በመካከላቸው ነበረች›› ብሎ የጻፈ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

ጌታችን ልጅነትን የምናገኝበትን ሥርዓ ጥምቀት አስቀድሞ በግብር ፈፅሞ ምሳሌ በመሆን ኋላ በቃ ከውኃና ከመንፈስቅዱስ ካልተወለዳችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ልትገቡ አይቻላችሁም እንዳለ፤ በመስቀሉ ላይ በዮሐንስ አማካኝነት በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ‹‹እነኋት እናትህ›› ‹‹እነሆ ልጅሽ›› ብሎ በቃሉ እናት አድርጎ ከመስጠቱ በፊት ከእርሷ በመወለዱ ልጆቿ አድርጎናል፡፡ ሊቃውንትም የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ በመሆኑ እኛን በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች አደረገን ‹‹ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ. . .›› እንዲል፤ ከድንግሊቱም ተወለዶ የድንግሊቱ ልጆች አደረገን ብለው አመስጥረውታል፡፡የዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ ማቴ1፥25-ፍጻሜ

ጌታ ቅድመ ዓለም አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ ከአብ እንደተወለደ፤ ድኅረ ዓለም ደግ ከእመቤታችን ፍጹም የሰውን ባህርይ በመያዝ በግዘፍ አካል ነስቶ ተወልዷል፡፡‹‹ንሕነ አባላቲሁ ለክርስቶስ››እ የክርስቶስ ብልቶቹ(አካሉ)ነን እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ በምሥጢር የክርስቶስ አካሉ የምንባል ክርስቲያኖች ሁሉ ከእርሷ ተወልደናል፤ እናትነቷም ተሰጥቶናል፡፡ ‹‹እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ›› ‹‹ሰው እናታችን ጽዮን ይላል ከእርሷ ሰው ተወልዷልና›› ዳለ ክቡር ዳዊት ከአዳም በሥጋ የተወለደ ሁሉ እንደሞተ፤ ከእርሱ(ከክርስቶስ) በመንፈስ የሚወለድ ሁሉ ለዘላለም በሕይወት እንዲኖር ከእርሷ ተወልዷልና ሰው እመቤታችንን ጸወነ ሥጋ ጸወነ ነፍስ(የነፍሳችንና የሥጋችን መጠጊያ መጽናኛ) እናታችን ሲላት ይኖራል ሲል የተናገረው ሁሉ በዚህ ተፈጽሟል፡፡1ቆሮ6፥15፤1ቆሮ12፥12-27፤መዝ86፥5

እመቤታችን በክርስትና ካላት ቦታ በትንሹ ይህ ካልን በልጇ አምን ክርስቲያን የተባልን ሁላችን ከእናትነቷ ምን ተምረናል? በወንጌል ከተገለጠው የእመቤታችን ሕይወት ምን ወስደናል? በእርግጥስ እንደ እናትነቷ እኛ የክርስትና ሕይወት ለእርሷ ደስታ የሚሆን ነው? የሚለውን ማንሳት ያስፈልገናል፡፡

ይህንን እንድናነሳ ያስገደደን በአብዛኛው ስለ እርሷ በማስተማር እንጂ ከእርሷ ፍጹም ልዩና የተቀደሰ ሕይወት ስንማር አንታይምና ነው፡፡ከእመቤታችን ሕይወት ልንወርስ የሚገቡንን  አርአያ ቅድስና (መልካም ነገሮች) መንፈስ ቅዱስ በዘመናት በሊቃውንት አንደበት በቅዱሳን ሕወት አድሮ እንዳስተማረን ሁሉ ከእርሱ የተቀበልነውን እንዲሁ እናቀብላለን፡፡

1ኛ. ትህትና፡- በእመቤታችን ሕይወት የምናየው በቃላት ከመገለጽ በላይ የሆነ ትኅትና ነው፡፡ ሊቃውንት ወትሮም እመቤታችን መጽሐፈ ኢሳያስን ስታነ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙን አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› ብሎ ከተናገረው ብትደርስ እኔ በሆንኩ አላለችምከዚች ድንግል ደርሼ ወጥቼ ወርጄ ባገለገልኳት አለች እንጂ፡፡ ኢሳ7፥14

ዛሬ ክብርን ሁሉ የከፍታ ወንበርን ሁሉ ለራሱ የሚመኝ እንጂ ለሀገር ለቤተክርስቲያን እንዲህ የሚራ ተነስቶ እኔ አገልጋዩ ሆኜ ባለፍኩ የሚል ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ ይህን የእመቤታችንን የትኅትና ሕይወት ማስተዋል ያስፈልገናል፡፡ተመርጠው ለክብር የሆኑትንም ስናይ ቀርቦ ማገልገል እንጂ መተቸት ለውጥ አያመጣም፡፡ ዛሬ ሁላችን የምንጨነቅ ሌላውን ስለመለወጥ እንጂ ስለራሳችን መለወጥ አይደለም፡፡

የእመቤታችን ትኅትና በመልአኩ ብስራትም ተገልጸ_ል፡፡ ያንቺ ጽንስ እንደ ሌሎች ሴቶች አይደለም ካንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ባላት ሰዓት‹‹እነሆ የጌታ አገልጋ (ገረዱ)እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› በማለቷ ታውቋል፡፡ እናቱ ትሆኛለሽ ሲላት ለልጇ አገልጋዩ መሆንዋን በመግለጽ ነበር ትኅትናዋን ያሳየች፡፡

ጌታ በመስቀል ሳለ ለዮሐንስ ‹‹እነኋት እናትህ››ለእመቤታችንም ‹‹እነሆ ልጅሽ›› ብሎ ሲያረካክባቸው፤ ከጌታ ጋር ኖሬ አገልጋይ፣ ከመምህር ጋር ኖሬ ከደቀመዝሙር፤ ከፈጣሪ ጋር ኖሬ ከፍጡር  አላለችም ዮሐንስ ወደ ቤቱ ሲወስዳት በትኅትና ተቀለች እንጂ፡፡ ስንቶቻችን ይሆን ከታናናሾቻችን ጋር እነርሱን መስለን መኖር የምንችል? ከታላላቆች ጋርማ ማንነታችንን ሸጠን ክብራችንን ጥለን እምነታችንን ሰውተን አንገታችንን እንደከዘራ ቆልምመን መኖርን እናውቅበታለን፡፡ ለፍርፋሪ ስንል!!!


 

2ኛ.ይማኖት፡- ከወላዲተ አምላክ ማርያም አንዱ የተማርነው ይማኖ ነው፡፡ከእርሷ በፊት ያልሆነ ከተፈጥሮ ርዓት የተለየ ያለወንድ ዘር መነስ እና በድንግልና መውለድ በመልአኩ ሲነገራትና ይህ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ሲላት ፈቃዷን በይማኖት ገልጣለች፡፡ ፍጹም እምነት ማለትም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ብሎ ማመን ነው፡፡

በቃና ዘገሊላ ርግ ለልጇ የወይን ጠጅ ማለቁን ከነገረችው በኋላ ላገልጋዮች በፍጹም እምነት የሚላችሁን አድርጉ ብላቸዋለች፡፡ በዚያ ደቂቃ ለዚያ ሁሉ ርገኛ የሚሆን ወይን ከየት ያመጣል? ምን መፍትሄ ሊኖር ይችላል?የመሳሰሉት የጥርጥር ሀሳቦች በእርሷ ዘንድ አልነበሩም፡፡ ሁሉን ቻይ መሆኑን ከቀድሞም አውቃና አምና ትኖር ነበርና፡፡

ዛሬ ያለውለም አካሄድ በእምነት ካልሆነ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ ጨለማው የማያልፍ ደመናው የማይገ የሚመስላቸው ብዙዎች ይኖራሉ፡፡ እምነት ማለት በእግዚአብሔር ኃይል የማይቻለው ይቻላል ሆን የማይመስለው ይሆናል ብሎ ማመን ነው፡፡ የተፈጥሮ ህግ፣ አመክንዮ ወዘተ… እዚህ ቦታ የላቸውም፡፡ የእርሱ ሥራ ከዚህ ሁሉ በላይ ነውና፡፡

3ኛ. ፍጹም ታዛዥነት፡- እመቤታችን ፈቃዷ ሁሉ ለልጇ የተሰጠ ነበር፡፡ ከእርሱ የተለየ ሀሳብ ወይም ፈቃድ አልነበራትም፡፡ ራሷን ፈጽማ ለእግዚአብሔር ያስገዛች ብላቴና ስለነበረች የመልአኩን ብራት የተቀበ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም ራሷን በመስጠት ነው፡፡ ከቀደምት ነያት እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ሲልካቸው ሲጠራቸው ምክንያት በማንሳት ወደኋላ ለማለት የሞከሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር ለሚጠራን አገልግሎት መማራት ክብር እንደሆነ ሁሉ ታላቅ ሸክምና ላፊነትም ነው፡፡ እመቤታችን ለእናትነት ስትመረጥ ታላቅ ክብር መሆኑ ቢታወቅም ‹‹በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል›› እስኪባል የደረሰ ታላቅ ላፊነትም ነበር፡፡ በፍጹም ታዛዥነትም እስከ ፍጻሜ ኃላፊነቷን ተወጥታለች፡፡ በመጨረሻም በመስቀል ላይ ሳለ በፈቃዱ ወደ እርሱ እስኪወስዳት ድረስ በዮሐንስ ዘንድ እንድትኖር ሲነግራት በጊዜው ወድቆባት ነበረ ነፍስን የሚወጋ ሀዘን ቃሉ ያላትን ታዛዥነት አልለወጠውም፡፡ 

4ኛ.ጥበብ መንፈሳዊ፡- እመ አምላክ ብራተ መልአክን በተቀበለችበት ወቅት ቅዱስ ገብርኤልን ትጠይቀው የነበሩ ጥያቄዎች ፍጹም ጥበብ መንፈሳዊ የተሞነበሩ፡፡ ከጉባዔ ያልዋሉ ምሥጢር ያላደላደሉ የመጽሐፍ ቅዱስ የከንፈር ወዳጆች የእመቤታችንን ጥያቄዎች የጥርጥር ያለማመን አድርገው ሲያቀርቡ እነሆ እንሰማቸዋለንእኒህ የወንጌሉ ምሥጢር የተከደነባቸው ናቸው፡፡እመቤታችን የጠየቀቻቸው ጥያቄዎች የተገቡና ነገረ ሥጋዌን የበለጠ እንዲብራራ ያደረጉ ናቸው፡፡ እመቤታችን ጥያቄዎቹን ባትጠይቅ ኖሮ፡-

    ሀ. ከእርሷ የሚወለደው ቅዱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ

    ለ. በድንግልናና ያለወንድ ዘር የተጸነሰና የሚወለድ መሆኑ

    ሐ. ለአበው በተሰጠው ተስፋና በትንቢ ነቢያት መረት የዳዊት ዘር መሆኑና የያዕቆብን ወገን ለዘላለም የሚገዛ መሆኑ፡

    መ. ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መለዱ በግብረ መንፈስ ቅዱስ መሆኑ

    ሠ. አብ ሊያፀናት ወልድ ለተዋሕዶ(ሥጋን ለመንሳት)መንፈስ ቅዱ ፍል ሊያዋሕድ እንደሚያድሩባት ተለይቶ ባልታወቀ ነበር

    ረ. የሚወለደው ሕጻን ስሙ ኢየሱስ እንደሚባልና ሕዝቡን ሁሉ ከጢአት ከመርገም ከፍዳ የሚያድናቸው መሆኑ

    ሰ. ራሷ እመቤታችን በንጽሕናና በቅድስናዋ ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የከበረች መሆኗ

    ሸ. ነቢ ልዑል ዐርኩ ለመርዓዊ የተባለ የሐንስ መጥምቅ በእግዚአብሔር ድንቅ ተዐምራት ከዘካርያስና ከኤልሣቤጥ መፀነስ፤ኤልሳቤጥ በብፅዐት ብትሰውረውም የተገለጠ በእመቤታችን ጥያቄ ነው፡፡

          ብዙ ጠይቀን ጥቂት መልስ ለማናገኝ ለእኛ የጥያቄ አቀራረብን አቅል(ሥርዓት) እንረዳበት ዘንድ ታላቅ ትምህርት ነው፡፡በአግባቡ ያልቀረበ ጥያቄ መልስ አይኖረውምና፡፡

5ኛ. መናፍስትን መመር፡-‹‹መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ››እንዲል፤እመቤታችን መልአኩ ተገልጦ የምስጋና ሰላም ባቀረበላት ጊዜ ወዲያውኑ አልተቀበለችውም፡፡መተርጉማን‹‹እናቴሔዋንን ያሳተ ሰይጣን…››ብላ አሰበች እንዲሉ ዛሬ ትንቢት ተናጋሪ፣ ራዕይ ተመልካችና ሕልም ሀላሚ በበዛበት ጊዜ፤ ብዙዎቻችንም በመናፍስት አራር የሚሆነውን ሳንመረምር በምናያቸው ድንቃ ድንቆች የሰዎችን እውነተኛነትና ቅድስና በምንመዝንበት ሰዓት ከተወዳጇ እናታችን እንዲህ ያለውን የመጠበቅ ጥንቃቄ ልንማር ያስፈልጋል፡፡1ዮሐ4፥1

6.ጭምትነት፡-እመቤታችን እንዴት ባለ ጭምትነት በንጽሕና በቅድስና እንዳደገች አባ ሕርያቆስ ሲናገር ‹‹ ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ›› ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ በማለት ገልጿል፡፡ ከቅዱስ ገብርኤል ከኤልሳቤጥና ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር በነበራት ጊዜ፤ ስምኦን አረጋዊ ጌታን ባቀፈውና ትንቢት በተናገረበት፤ በአሥራ ሁለት ዓመቱም በቤተ መቅደስ በጠፋባቸው ወቅት፤ እንዲሁም በጊዜ ስቅለቱ በደረሰባት ሀዘን ወዘተ…ጭምትነቷ በሚያስደንቅ ሁኔታ ታይቷል፡፡በእያንዳንዱ ሁኔታ ምታደርገው እንቅስቃሴም ሆነ ንግግር ፍጹም ጸጋን የተላበሰ ነበር፡፡ጥያቄዋ፣ ሰላምታዋ፣ ቅሬታዋንም ሆነ ሀዘኗን ትገልፅበት የነበረበት መንገድ በፍጹም ጭምትነት የተጌጠ ነበር፡፡ በመልአኩ እንደተነገራት በኤልሳቤጥም እንደተመሰከረላት የእስራኤል ተስፋ ከእርሷ እንደሚወለድ የታወቀ ቢሆንም ቸኩላ ይህን ምስጢር ለማንም አልገለጠችም፡፡ እርሱ በሚፈቅደው መንገድ ራሱን እስገልጥ በጭምትነት ጠበቀች እንጂ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞዎስ በክርስቶስ ላመኑ ክርስቲያን ሴቶች መክር የሚገባውን ሲነግረው ‹‹…ሴቶች ጭምቶች፣የማያሙ፣ልከኞች፣በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል›› ብሎታል፡፡ 1ኛ ጢሞ3÷11 ቅምጥሊቱ ሴት ግን በሕይወቷ ሳለች የሞተች ናትና፡፡1ኛ ጢሞ5፥8 የክርስቲያን ሴቶች በራቸውም ሆነ በአነጋገራቸው በአለባበሳቸውም ሆነ በአካሄዳቸው ራሳቸውን በጭምትነት እንዲገልጹ ከእመቤታችን በላይ አርአያ ሊሆን የሚችል አሰጣቸውም፡፡


 

7. በራዊ ሕይወት፡- እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የኤልሳቤጥንመነስ ከመልአኩ እንደሰማች ፈጥና ነው ወደ ኤልሳቤጥ የሄደችው፡፡ ያቺ እግዚአብሔርን በመፍራት የምትኖር የካህን ሚስት ስለቷ ተሰምቶ በመልአክራት ወንድ ልጅ መነሷን ስትሰማ ደስታዋን ለመካፈል አልዘገየችም፡፡ በሰው ሀዘን ተደስቶ በባልንጀራው ደስታ የሚከፋ በበዛበት በዚህ ክፉ ዓለም የእርሷን አርአያ መከተል ምንኛ መቀደስ ነው፡፡ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፣ሚያዝኑ ጋር አልቅሱ››ያለ የሰውን ስሜት በቅንነት መካፈልክርስቲያናዊ ምግባር በመሆኑ ነው፡፡ሮሜ 12፥15፤ ሉቃ 1፥57-65

          ከእግዚአብሔር የሆነን ነገር ደግሞ የሰዎቹን ደስታ ከመካፈል ባለፈ ማድነቅ ይገባል፡፡ለኤልሳቤጥ ከእግዚአብሔር እንደሆነው ሁሉ ለሕዝቡ ጥቅም ከእግዚአብሔር የሆነ ስጦታ(ጸጋ) የተሰጣቸው ስንመለከት

ሀ. እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ ስለሠራው ድንቅ ሥራ

ለ.እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ ሕዝቡን ስለመጥቀሙ

ሐ.በዘመናችንም ዓይኖቻችን የእርሱን ድንቅ ሥራ በማየታቸው ልንደሰት ይገባናል፡፡ ከእግዚአብሔር በሆነ ጸጋ መቅናት፤ሰዎቹ ሩት ሥራ እንቅፋት መሆን ከእግዚአብሔር ጠላቶች ጋር መሰለፍ ነው፡፡

8. ድንግልና፡- የእመቤታችን ድንግልና፡-

ሀ. በሥጋ በኅሊና በመሆኑ( ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ) እንዲል

ለ.ሕዋቶቿ በሙሉ የተጠበቁ መሆናቸው ማለት የኃጢአት መግያ ከሆኑት ከርዕይ ከሰሚዕ ከገሢሥ ከአንዎ የተጠበቀች መሆኗ( ከማየት፣ከመስማት፣ከመዳሰስ፣ከማሽተት)

ሐ.ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ፤ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግልናዋ ለቅጽበት ያልተለወጠ መሆኑ(ድንግልናዋ እናት በመሆኗ ያልተለወ መሆኑ)ልዩ ያደርጋታል፡፡ይህ ለሌሎች ሴቶች አይቻልምና‹‹ከሴቶች ተለይተሸ››ያሰኛት ቅሉ አንዱ ይህ ነው፡፡

          በተፈጥሮ ርዓት አንዲት ሴት ሙሽራዋን እስክታገኝ(እስኪመጣ)ራሷን በመግዛት እንደምትጠብቅ፤ ያ ካልሆነ ግን ከክብር እንደምታንስ በመንፈሳዊው ይወትም ነፍሳችንን በኃጢት ከክብር ከማነስ ጠብቀን ድንግልና የተባለ ልጅነታችንን በሃይማኖት በምግባርሙሽችን የሆነው ክርስቶስ እስኪመጣ እንጠብቃለን፡፡

ለእርሱ ለክርስቶ የሸለመች ሙሽራ ሆነን እንዴት ባለ የነፍስ ቅድስና መጠበቅ እንዳለብን የተሰጠችን ሕያው ምሳሌ ደግሞ እመቤታችን ነች፡፡ በእርሷ በአካል ያደረ በእኛ በጸጋ ያድርብናልና፡፡የዮሐ.ራዕ 21፥2

9.ጸሎት፡- እመቤታችን የመልአኩን ብሥራት የኤልሳቤጥንና የዮሐንስን ምሥክርነት ከተቀበለች በኋላ የተናገረችው ጸሎት ዘመናት በአላውያን ነገሥት በአረማውያን እንዲሁም በመናፍቃን የተነሣባትን የጥፋት ማዕበል ለመሻገር ለቤተክርስቲያን ጉልበት የሆነ ነው፡፡ጸሎቷም ምን ያህል በቅዱሳት መጽሐፍት እውቀት የበለጸገ የልዑሉንም ሥራ በማስተዋል የከበረ መሆኑ ተገልጦ የሚታይ ነው፡፡  ፍጹም በነፍሷ ለእግዚአብሔር ያላትን ክብር፣ ትኁታኑን ማይረሳ መሆኑን፤ ቅድስናውን፣ እውነተኛ ፈራጅ መሆኑን፣ለሚፈሩት የሰጣቸውን ቃል ኪዳን የማይረሳና ምህረቱም ለልጅ ልጅ መሆኑን የገለጠ ነው፡፡በከንፈ እግዚአብሔርን የሚያከብሩና በነፍሳቸው ልዑሉን የሚፈሩ የጸሎታቸው ልዩነት ለማነጻጸር ከሚቻል በላይ ነው፡፡ ጸሎተ ማርያም ዛሬም ድረስ በቤተክርስቲያን ለካህናት ሞገስ ለሕሙማን ፈውስ፤ ለሀገር ሰላም ለርኁባን ምግብ፤ለመምህራን ጽናት ለደቀመዛሙርት እውቀት የሆናቸው ለዚህ ነው፡፡ሐዋርያትም በጸሎታቸው ወቅት እርሷን ይዘው መጸለያቸው የጸሎታቸው ምላሽ ይፈጥን ዘንድ ነው፡፡የእርሷ ጸሎት ተሰሚ ጉዳይ ፈጻሚ መሆኑን በቃና ርግ በግልፅ ማት ይቻላል፡፡ ‹‹የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም››ብላ ለልጇ ከነገረችው በኋላ ድጋሚ መጠየቅ አላስፈለጋትም ‹‹የሚላችሁን አድርጉ›› አለች እንጂ፡፡ ደራሲ‹‹አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንሌኪ ድንግል ዘየዐርግ ሉዐሌ››ያለ ይህን ማስተዋል በመቻሉ ነው፡፡በመሆኑም እመቤታችንን ሳትይዝ ጸሎት ልመና አቀርባለሁ የምትል ቤተክስቲያን ብትኖር እርሷ ሐዋርያት የሰበሰቧት ቤተክርስቲያን አለመሆኗ በዚህ ይታወቃል፡፡

0. ምስጋና፡- እመቤታችን በእርሷ ላይ ይሆን ዘንድ ልዑሉ የፈቀደው ከሆነ በኋላ ይን የተረዱ እነ ኤልሳቤጥ ተፀውዖ ስሟ ማርያም ብለው መጥራታቸውን እንደማይገባ ድፍረት አድርገውስለቆጠሩት፤ የእርሷም ከቤታቸው ጣሪያ በታች መግባት የተገባቸው እንዳልሆነ ስለተረዱት‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?››በማለት ክብሯን ገልጠው መሰከሩ፡፡እቤታችን ጌታን ፀንሳ ከወለደች በኋላ በወንጌል እንዲሁ ‹‹ማርያም›› ተብላ ስትጠራ አናገኝም፡፡ወንጌላውያኑ ሁሉ ‹‹የሕጻኑ እናት›› ‹‹የኢየሱስ እናት›› ‹‹ሴቲቱ››እያሉ ሲጠርዋት ነው የምናየው፡፡ ሁሉም መጠሪያዎች የነቢያትን ትንቢት መፈጸም የሚያሳዩና የሥጋዌን ምጢር ያዘሉ ናቸውና፡፡ይህን የተረዱ ሊቃውንት‹‹እመ አምላክ፣ ወላዲተ አምላክ፣እመ ብርሃን ወዘተ…››እያሉ መጥራቻቸው ወንጌላውያንን አብነት አድርገውነገ ሥጋዌን ለመግለጽና ክብሯን ለመመስከር ነው፡፡

          እመቤታችን በኤልሳቤጥ ቤት ሆነውን ካየች በኋላ‹‹ለእኔ(በእኔ)ታላቅ ሥራን አድርጓልና ስም ቅዱስ ነው›› ስትል አመስግናለች፡፡ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስብሎ ማመስገን በዓለ መላእክት የተለመደ ነው፡፡የመላእክት እህት የሆነች እመቤታችንም ከነፍሷ የሆነ ምስጋናዋን በዚሁ ሰማያዊ በሆነ ምስጋና ገልጻለች፡፡ ይህም ከመላእክት ጋር የነበራትን የምስጋና ኅብረት ያሳያል፡፡ከዚህም በግላችንም ሆነ ለፍጥረተ ዓለም ለተደረገው የእግዚአብሔር የቸርነቱ ሥራ ማመስገን የተገባ መሆኑን ለሁላችን ትምህርት ትታልናለች፡፡

እመቤታችን ፈጣሪዋናአምላኳ እንዲሁም ልጇ የሆነውን እርሱን ማመስገን ብቻ ሳይሆን፤በእርሷ ላይ በተደረገው ድንቅ ነገር ትውልድ ሁሉ ሲያመሰግኗት ሲያደንቋ እንደሚኖሩም ገልጻለች፡፡በዚህም የተነሳ እውነተኛዋ የሐዋርያ ቤተክርስቲን ልዑል እግዚአብሔርን ከማመስገን ለጥቃ  እመቤታችንን በውዳሴ በቅዳሴ በማንሳት ታመሰግናለች፡፡ ልጆቿም በነገር ሁሉ በንጽሕናና በቅድስና በማጌጥ እናታቸውን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲመስሉ ታስተምራለች፡፡ ቤተክርስቲያን በማኅሌቱ በቅዳሴው በሰዐታቱ በስብከቱና በትምህርቱ ሁሉ ደጋግማ እመቤታችንን የማንሳቷ ምስጢር በንጽሕናና በቅድስናዋ አብነት በመሆን በአማላጅነቷም ፍጹምነት ወደ እግዚአብሄር እቅፍ የምታደርሰን በመሆኗ ነው፡፡

ከጥንት ሲወርድ ሲወራረድ የመጣው ትክክለኛ ዶግማ ኖናና ትውፊት እንዳይበረዝ እዳይከለስ በማስተማር ጠብቃ ማቆየቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ከማንም በላይ ሐዋርያት ከጌታችን የተቀበሉት የጥንታዊውና የእውነተኛው ክርስትና የታመነችባለ አደራ ቤተ መዘክር ያደርጋታል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

                                               እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሰን!

                                                                 ቀሲስ ታምራት ውቤ

ነሐሴ 2007 ዓ.ም

Read more...

ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ክፍል ስምንት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በተለያዩ አህጉር ተበትናችሁ በቃሉ ለመኖር ለምትጋደሉ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ ህሊናን ሁሉ የሚያልፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በሚል ቃለ ብሥራት ሰላምታችንን እያስቀደምንና በትንሣኤው ትንሣኤያችንን እያወጅን ሰነበትን፡፡ “በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፈንታ ደስ ይለናል፡፡” እንዳለ ነቢዩ ዳዊት ፍርድህን ከሰማንበት ቃልህ፤ ምህረትህን ፣ ይቅርታህን ፤በሞት አዋጆች ፈንታ ትንሣኤና ሕይወትን፤ከባርነት ተላቀን ነፃነትን በመቀዳጀታችን የመከራውን ዘመን አስረስተህ ደስታን ሞላኸን፡፡ ከዛሬ ፪ሺ ዓመት ገደማ የበዛልን ሥጦታህ ከአበው ወደ ውሉድ እየተላለፈ ደስታው ሳይፈዝ ስሜቱ ሳይደበዝዝ “ግበሩ በዓለ በትፍስህት” እንዲል ዛሬም እንደያኔው አከበርነው፡፡ ሰውነታችን በፆም እንዳከበረችህ በመብልም አመሰገነችህ፡፡ በድካማችን፣በትካዜያችን፣በረሃብና በጥማችን፣ በሀዘንና በዕንባችን ወራትም ትዝታችን አንተ ነበርህ፤ በደስታና በሐሤት በመብልና በመጠጥ ወራትም የአንደበታችን ቅኔ የዝማሬያችን ጉልበት አንተው ነህ፡፡

በምሴት ይደምፅ ብካይ ወበጽባህ ፍስሐ” እንዳለ ክቡር ዳዊት በጨለማ ኦሪት፣ በጨለማ ኃጢአት በጨለማ ሞትና ሲዖል በተያዝንበት ወራት አለቀስን፤ የወንጌል ብርሃን፣ የትንሣኤ ብርሃን፣ የጽድቅ ፀሐይ በወጣበት ዘመን ሐሤት እናደርጋለን፡፡ የፊትህን ብርሃን አይተናልና ቀኑን ሁሉ ደስ ይለናል፡፡ ይኸውም በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያገኘነው ዘላለማዊ ይቅርታህ ነው፡፡

ከላይ ያልነውን ሁሉ ያልነው ስለ ዐብይ ፆም ሰንበታትና ስለ ጌታችን ስቅለት ትንሽ ጽፈን ስለነበር ምነው ትንሣኤውስ? ላለመባል ነው፡፡ ትንሣኤ ካልታወጀ ካልተሰበከ ክርስትና ተብሎ ነገር የለምና፡፡ ትንሥኤውንም የማያምንና የማይሠብክ ሰውም ከመላእክት አንድነት ሊጨመር ከነቢያትና ከሐዋርያት ከጻድቃንና ከሰማዕታት ኅብረትም አንድ ሊሆን አይቻለውም፡፡ የኒህ ሁሉ መከራቸው በትንሣኤው ማመናቸው ክብራቸው ትንሣኤውን መመስከራቸው ነውና፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ሉቃ 241-8 1ቆሮ 151-ፍፃሜ

ዐብይ ፆም በነገሠባቸው ሁለት ወራት ስለጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክነት በተከታታይ እናቀርበው የነበረውን ትምህርታዊ ጹሑፍ በይክረም አቆይተነው ነበር፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ቀጥለን እንጽፋለን፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ” ይላል፡፡ ክብር ሁለት ወገን ነው፡፡ አንዱ የባህርይ ሲሆን ሌላኛው የጸጋ ክብር ነው፡፡ ሮሜ 137

.የባህርይ ክብር የጌታ እግዚአብሔር የብቻው ነው፡፡ ማንም ማን በዚህ ሊመሰል፣ሊጠራ ሊታመንና ሊመለክ አይችልም፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ሿሚ የሌለበት ንጉሥ፤ አክባሪ የማይሻ ክብሩ ነው፡፡ ሌላው ፍጡር ሁሉ ቢነግሥ ቢከብር ወደው ፈቅደው ወይም ተገደው ተዋርዶ ባገኛቸው ላይ ነው፡፡ ሕዝብ ከሌለ ንጉሥ ተገዢ ሳይኖርም ገዢ አይኖርም፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ግን ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ንጉሥ ነው፡፡ “እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም” እንዲል ክቡር ዳዊት፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም በቅዳሴው“ ከዓለም አስቀድሞ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር በመንግሥቱ በሦስትነቱ በአምላክነቱ ነበር” በማለት ገልጾታል፡፡

በዚህ ክብር ሊጠራ ሊመሰገን የሚችል አልነበረም አይኖርምም፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም በማለት አስጠንቅቋል፡፡ ይህ ከሆነ ዘንዳ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለፈጣሪ በሚገባና በሚቀርብ ክብር ምስጋና ማክበር ተገቢ ነውን? መልሱ “ይደልዋ ” ወይም “ይገባወል” ነው!

- ዮሐ 114-18….አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን…መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው ” በዚህ ቃል የእርሱ ክብር ከአባቱ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር ፍፁም አንድ አንደሆነ ተረዳን፡፡ ለፍጡር እንዲህ ይባል ዘንድ ከቶም አይቻልም፡፡

- ማቴ 1627- የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና…..የሚለውም ከላይ ያለውን የሚያጠናክር ነው፡፡

- የፈጣሪ ምስጋና ለፍጡር አንደማይሠጥ የክርስትና ጽኑዕ ሕግ ነው፡፡ በራዕየ ዮሐንስ ም 56-14 ያለው ሰማያዊ የቅዳሴ ሥርዓት ስንመለከት መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤል ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች ሱራፌል እልፍ አእላፋት መላእክትም በተባርዮ(እየተቀባበሉ) “…በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን!አሜን!” እያሉ ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ፍጡር ቢሆን በሰማያዊያን መላእክት አፍ ይህን ምስጋና ባልተቀበለም ነበር፡፡ “በጉ” የሚለው የሚወክለው እርሱን ነውና፡፡ ራሱ ጌታችን በተናገረው “አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አክብረኝ” ማለቱ በቅድምና በክብር መኖሩን ያሳያል፡፡ ፍጥረት ያልነበረበት ጊዜ እንደነበርም እናውቃለንና፤ከፈጣሪ በቀር ቅደመ ፍጥረት በክብር ሊኖር የሚችል ማን ሊኖር ይችላል? ዮሐ 175

- የባህርይ ክብር ወይም አንድን ነገር የባህርይ ነው ስንል ከማንም በሥጦታ ያልተቀበልው ፍቅር ሲሆን የሚጨመርለት ከፈቃድ ሲወጣ የሚቀነስበት ያይደለ ሰጭም ሆነ ነሺ የሌለበት ማለት ነው፡፡ ፍጡራን ሁሉን የተቀበሉ ከፈጣሪ ልግስና ነው፡፡ በድካም በጥረት በዋጋ ስላላገኙት “በጸጋ(በስጦታ)” ተብሎ ይገለፃል፡፡ ከፈጣሪ የተቀበልናቸው ሥጦታዎች ሁሉ በዋጋ የማይተመኑም በመሆናቸው በጸጋ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አንድም ጠይቀን ለምነን ያገኘናቸው ባለመሆናቸው ከልዑሉ ልግስና የተነሣ በጸጋ ያገኘናቸው እንደሆኑ እናምናለን፡፡

ለፍጡራን የተሠጡ ሁሉ በመታዘዝ ይጨመርላቸዋል ከፈቃድ ሲወጡ ይገፋፉታል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሰው በመሆኑ ቅድመ ዓለም ከነበረው ክብር የተቀነሰ ወይም የተጨመረ ነገር የለም፡፡ በሰዎች ዘንድ ብዙ ወርደትን መቀበሉም ፈቃዱን እንጂ በባህርዩ የጎደለበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡

ከትንሣኤ በኋላም የኤማሁስ መንገደኞችን ሲወቅስ “ክርስቶስ መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? ነው ያላቸው፡፡አዲስ ክብር አልተቀበለም የትህትናን ሥራ ሠርቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ገባ እንጂ፡፡ ይህም ሲባል አጥቶት(ተወስዶበት) ነበር መልሶ አገኘው ማለት አይደለም፡፡ በፈቃዱ ራሱን ዝቅ ማድረጉን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ራሱን ዝቅ ማድረጉ የፈቃድ እንጂ የባህርይ አይደለምና፡፡

በተጨማሪ እኒህን ጥቅሶቸወ ተመልክተው ያገናዘቡ፡፡

ማቴ 2531 የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፡፡

ዮሐ517-18፤ ዮሐ1030-37፤ ዮሐ148-11 1ጴጥ 4112ጴጥ 318

- የክብር ባለቤት እንደመሆኑም በአፈ መላእክት ወሰብዕ በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም በታች ያለ ፍጥረት ሁሉ ያመሰግነዋል ለአምላክነቱም እንደሚገባ ይሰግድለታል፡፡

- ማቴ211- የጥበብ ሰዎች በቤተልሔም በእናቱ እቅፍ ሲያገኙት እጅ መንሻ በማቅረብ ሰግደዋል፡፡

- ዮሐ91-ፍፃሜ፡- ባለው ውብ ታሪክ ላይ ጌታ ዓይኑ ይበራለትን ሰው አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህ? ሲለው አምን ዘንድ እርሱ ማነው? በማለት መልሶ ጠይቆታል፡፡ ጌታም አይተኸዋል የሚያነጋግርህም እርሱ ነው ባለው ጊዜ አምናለሁ ጌታ ሆይ በማለት ሰግዶለታል፡፡

- ማቴ1433- በባህር ላይ እየተራመደ ሔዶ ወደ ታንኳዋ በገባ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ሰግደውለታል፡፡

- ብዙ ዓሣ ባጠመደ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ፤ ደሟ በቆመ ጊዜ ሴቲቱ፤ ልጁ የሞተችበት ኢያኢሮስም ለጌታችን ሰግደውለታል፡፡ ሉቃ 58፤ማር 533፤ ማር 523

- በትንሣኤው ጊዜ የገሊላ ሴቶችና ደቀመዛሙርቱ ሰግደውታል፡፡ ማቴ 289 እና 17

- ራዕ 511-14፡ አየሁም በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎችም ዙርያ የበዙ መላእክትን ድምጽ ሰማሁ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፡፡ በታለቅ ድምጽም የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋና በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ፡፡በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባህርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፡፡በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ አራቱም እንስሶች አሜን አሉ፤ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ፡፡

በዚህ ጥቅስ ላይ እንደተመለከተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ(የእግዚአብሔር በግ) በፍጡራን ሁሉ አንደበት ተመስግኗል፡፡ ሦስት ነገሮችንም እንመለከታለን፡፡

. ምስጋናና ክብር ይገባዋል የተባለው ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፡፡ መነሻና መድረሻ ጥንትና ፍፃሜ የሌለው ከዘላለም እስከ ዘላለም በምስጋና በክብር ተፈርቶ የኖረ ከርሱ በቀር የለምና፡፡

. ምስጋናና ክብር የቀረበለት ከባህርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ተካክሎ ነው፡፡ ከፈጣሪ ጋር ተካክሎ(ተጫፍሮ) በአንድ ምስጋናና ክብር ሊቀርብለት የሚችል ፍጡር ደግሞ ሊኖር አይችልም፡፡

. የመከራ የስደት የረሃብ የጥም የሞት የእስራት ፍርሃት ስጋት የሌለባቸው፤እበላ እጠግብ እሾም እሸለም ብለው የማያጎበድዱ፤የልዑሉን ፈቃድ ብቻ የሚፈፅሙ ኪሩቤል ሱራፌልና አጠቃላይ መላእክት በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም መስገዳቸው አምላክነቱን ቢያውቁ አንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

ፊልጵ 25-11 “…እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ…(እስከ ቁጥር 11 ይፃፍ)



የመንፈሳዊው ዓለም ነዋሪዎች መላእክት ተፈጥሯቸው ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ለመራባት፣በመድከም ለመዘንጋት፣ ለሀብት መጓጓት፣ ለመሞት ወዘተ…ተላልፎ ያልጠሠጠ፤ታናሹን ማዋረድ ለታለቁ ማጎብደድ የሌለባቸው ለአንዱና በጌትነቱ ብቸኛ ለሆነው አምላክ በፍፁም ኃይላቸውና በፍፀም አሳባቸው የሚገዙ የሚያገለግሉም ደገኛ ፍጥረት ናቸው፡፡

መላእክቱ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ” መዝ 102(03)20፤“መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዩቹን የእሳት ነበልባል” መዝ 9011፤“አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ” ትን.ዳን 622 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ…መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ…መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና“ ዘጸ 2320 ላይ የተጠቀሱ ሀሳቦች የመላእክት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ እርሱም ፈቃዱን ይፈፅም ዘንድ ለመዓትም ሆነ ለምህረት ይልካቸዋል፡፡ ስሙን ተሸክመው ስለሚሄዱ ባለሙሉ ሥልጣን ናቸው፡፡ ሉቃ 119 የጌታን ፈቃድ ይፈፅማሉ እንጂ የረሳቸው ፈቃድ የላቸውም፡፡ለሌላም አይገዙም፡፡ ዘፀ 2321

ከላይ ባየናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አሳቦች የእግዚአብሔር መላእክት የተባሉት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መልእክተኞችና አገልጋዩች እንደሆኑም ተመዝግቧል፡፡

- ማር 113-…መላእክቱም አገለገሉት” ፤መላእክት አላለም መላእክቱ እንጂ፡፡

- ማቴ 1341-“የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፡፡”

- ማቴ2430-31- “…የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፡፡

መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፡፡

አንዳንዶች በራዕይ 127 ላይ የተመዘገበውን በመያዝ ሚካኤልና መላአክቱ ሰለሚል ከዚህ የተለየ ትርጉም አይሠጠውም ይላሉ፡፡ምክንያቱም ሚካኤልና መላእክቱ ማለቱ ቅዱስ ሚካኤልን የመላእክት ጌታ(የአምላክ) አያደርገውምና፡፡

በዚህ ምንባብ ሚካኤልና መላእክቱ የሚለው ቃል ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ መሆኑን ለማመልከት እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ዳን 211 ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱን ሀሳቦች ዓይነተኛ በሆነ መንገድ የሚያስታርቃቸውና ልዩነታቸውን የሚያሳየን ከዚህ የሚከተለው ምንባብ ነው፡፡

- ዕብ 11-ፍፃሜ፡- ቅዱስ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመላእክት በኩል ያለውን ልዩነት ባብራራበት መልእክቱ ከመላእክትስ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ደግሞም እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ፡- የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል፡፡

የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም” ሲል ቅዱስ ሚካኤልንም ጨምሮ መሆኑ የተረዳ ነገር ነው፡፡ በኲር፣ የሰው ልጅ፣ በግ ወዘተ…ተብሎ የተጠራው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምስጋና የተገባው በእግዚአብሔር ዙፋን እስኪቀመጥ የከበረ፣ መላእክት የሰገዱለትና ፍጥረታት ሁሉ ያመሰግኑት ፍፁም የባህርይ አምላክ ቢሆን አይደለምን? በዚህም የመላእክት ጌታ መሆኑን አወቅን፡፡

- ራዕይ 226-7- ላይ “…የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ፡፡ “የሚለውን በዚሁ ምዕራፍ ቁጥር አስራ ስድስት ከተፃፋው ጋር ሲነፃፀር ኢየሱስ ክርስቶስ የመላእክት አምላክ ጌታ ፈጣሪ እንርሱም ታዛዦቹ መልእክተኞቹ እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ቃሉ እንዲህ ይላል “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንደ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ፡፡”

ይቆየን!

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Read more...

ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ክፍል ሰባት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

መግቢያ፡ በተለያዩ አህጉር ተበትናችሁ በቃሉ ለመኖር ለምትጋደሉ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ ህሊናን ሁሉ የሚያልፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

ሌላው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክነቱን ከገለፀባቸው ባህርያት አንዱ ኃጢአትን የማስተሰረይ(ይቅር የማለት) ሥልጣኑ ነው፡፡

በመጽሐፍ እንደተፃፈ ኃጢአትን ማስተሰረይ ብቸኛ የቅዱስ እግዚአብሔር ሥልጣን ነው፡፡ በማር.ወን 25- ላይ ሽባውን ሰው እንዲፈውስላቸው በአልጋ አድርገውና የቤቱን ክዳን ነቅለው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ሲያቀርቡት አንተ ሰው ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ነበር ያለው፡፡ በዚያ የነበሩ አይሁድም "ይህ ሰው በርግጥ ይሳደባል ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ማን ይችላል?" በማለት ሲያጉረመርሙ ጌታችን ግን "የሰው ልጅ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው እንዲያውቁ አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡ ሽባውንም ፈውሶታል፡፡ እዚህ ላይ"የሰው ልጅ" እያለ ጌታ የሚጠራው ራሱን እንደሆነ አስተውል፡፡

ኃጢአት የሚሠራ ሰው በዋናነት የሚበድለው ቅዱስ እግዚአብሔርን ነው፡፡ ምክንያቱም፡

1. ሕጉን ይተላለፋል አድርግ የተባለውን ሲያስቀር አታድርግ የተባለውንም ሲያደርግ የአግዚአብሔርን ሕግ ማቃለሉ አይደለምን?፡፡ ለልዑል እግዚአብሔር ፍቅርና ክብር እንዳለን የሚታወቅበት ብቸኛ መንገድ በቃሉ(በሕጉ) ታዛዥ ሆነን መገኘት ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ዓመፀኞች ነን፤ ዓመፃ ደግሞ ኃጢአት ነው፡፡ ኃጢአትንም የሚያደርግ ከእግዚአብሔር አልተወለደም፤እግዚአብሔርንም አያውቀውም፡፡ 1ዮሐ 2

2. እግዚአብሔርን የሚበድለው የፈጠረውን ፍጥረት በማሳዘኑ ነው፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር የፍጡራኑ በደልና ሥቃይ የሚሰማው አምላክ ነው፡፡ ገዢያችን አባታችን ነውና፡፡ የግዛቱ መደፈርና የህዝቡ በጦርም ሆነ በምርኮ መንገላታት ንጉስን ከዙፋኑ አውርዶ ከቤተመንግስቱ አስወጥቶ ጦርነት እንደሚያስከትተው፤የሚስቱ የልጆቹ መጠቃት የአባትን ቁጣ ቀስቅሶ ለበቀል አንደሚያነሣሣው ለልዑል እግዚአብሔርም የፍጡራኑ መበደል አንዲሁ ነው፡፡ ከዚያም በላይ ከአካላችን አንዱ ብልት ላይ የሚደርስ አደጋ ህማሙ ነፍሳችን እንደሚሠማት ለጌታ እግዚአብሔርም በፍጡራኑ ላይ የሚደርስ ጥቃት እንዲሁ ነው፡፡

በመሆኑም ሰው ኃጢአት ሠርቶ ባልንጀራውን ቢበድል ይቅርታን ማግኘት ያለበት ከተበዳዩ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ከልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ምሳሌ፡- አንድ ሰው ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች ብላቴናን በግዳጅ ቢደርስባት ጥቃቱ(በደሉ) የእርሷ ብቻ ሳይሆን የቤተሰብ፣ የማኅበረሰቡና የመንግስት ጭምር ነው፡፡ ምንም እንኳ በዳዩ ሽማግሌ ልኮ ካሣ ከፍሎ ከተበዳይዋም ሆነ ከቤተሰቧ ይቅርታን ቢያገኝ የሀገሪቱን ሕግ በመተላለፉና በአንዲት ንፁህ ዜጋ ላይ ወንጀል በመፈፀሙ በመንግስት ሕግ ከመጠየቅ አይድንም፡፡ ማኅበረሰቡም ይህ ሰው ነገ ሊያደርሰው የሚችለው ተመሳሳይ በደል ሊታረም የሚችልበትን መንገድ ከመጠየቅ ችላ አይልም፡፡ ስለዚህ ያ ሰው ፍፁም ይቅርታን አግኝቻለሁ ብሎ በሰላም መኖር የሚችለው ከግል ተበዳይዋ፣ ከቤተሰቧ፣ ከማኅበረሰቡና ከመንግስት ይቅርታ ሲደረግለት ነው፡፡ በመንፈሳዊው ዓለምም ይኸው ነው፡፡ ሰው የግል ተበዳይን ብቻ ሳይሆን ቅዱስ እግዚአብሔርን ፍፁም ይቅርታ በሚጠይቅ ሰዓት ስርየትን ያገኛል፡፡ የአባቱን ሀብት ያባከነው ወጣት ወደቤቱ ሲመለስ ለአባቱ "በሰማይና በምድር ፊት በድያለሁ" ያለው ለዚህ ነው፡፡ በምድር ወላጅ አባቱን በሰማይ ያለ ፈጣሪውን በድሏልና፡፡ሉቃ 15

ስለዚህ በዚህ አግባብ ፍፁም የኃጢአት ይቅርታን ሊሠጥ የሚችል ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዳዊት " ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ አጥንቶቼ ሁሉ የተቀደሰ ስሙን ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል ከደዌሽ ሁሉ የሚፈውስሽ…"

በማለት የይቅር ባይነት ሥልጣን የቅዱስ እግዚአብሔር መሆኑን ይገልፃል፡፡ ጨምሮም…ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ" እንዲሁም "አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ አቤቱ ማን ይቆማል? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና" በማለት ያስረግጣል፡፡መዝ 311-5፣ መዝ1021-14፣መዝ 129(130)3

ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን የጌታ እግዚአብሔር መሆኑ ከታወቀ ኢየሱስ ክርስቶስ "ኃጢአትህ() ተሰረየችልህ()" ማለቱ እርሱ አምላክ(እግዚአብሔር) ለመሆኑ ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡

ሉቃ748- ሽቱ የቀባችውን ሴት በቃሉ "ኃጢአትሽ ተሰረዮልሻል በሰላም ሂጂ" ብሎ ሲያሰናብታት በዚያ የነበሩ "ኃጢአትን ስንኳ የሚያስተሠርይ ይህ ማነው? እስከማለት ተገርመዋል፡፡

ሉቃ2343- በመስቀል ላይ ሳለ በቀኙ የተሰቀለ ወንበዴ በሰማይና በምደር የተፈፀሙ ተዓምራቶችን አይቶ "በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ" ብሎ ላቀረበው የይቅርታ ልመና" ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" በማለት የይቅርታ ባለቤት መሆኑን አሳይቷል፡፡

ሉቃ2446-"ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፤በስሙም ንስሐና የኃጢአት ሥርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአህዛብ ሁሉ ይሰበካል"፡፡ ልናስተውል የሚገባን በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዓለም ሃይማኖቶች ታሪክ ንስሐና የኃጢአት ሥርየት በስሙ የሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ በቡድሐም፣ ሆነ በክሪሽና በዘራስተርም ሆነ በመሐመድ የለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም በቀደምት አበው ሆነ በነቢያት፣ በነገስታት ከጌታም በኋላ በተነሱ በሐዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታት ስም የኃጢአት ሥርየት አልተሰበከም፡፡ ሁሉ በእርሱ ከኃጢአት ነፁ ለዚሁም ምስክር ሆኑ እንጂ፡፡

የሐዋ.ሥራ 237-38- ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ጰራቅሊጦስ የሰበከውን የሰሙ ልባቸው የተነካ ሰዎች ምን እናድርግ ? ብለው በጠየቁ ሰዓት የተሰጣቸው መልስ "ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁ ይሠረይ ዘንድ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ" የሚል ነው፡፡

1ዮሐ11-10- ያየነውን እንመሠክራለን ያለ ዩሐንስ ወንጌላዊ "ኃጢአት የለብንም ብንል ውሸተኞች ነን … የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል…በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነ ጻድቅ ነው፡፡" በማለት የኃጢአትን ይቅርታ እንዴት እንደሆነ ጽፎልናል፡፡

ኃጢአትን ይቅር የሚል በደልን የሚደመስስ ለሚወዱትም መንግሥቱን የሚያወርስ ጌትነቱ በሁሉ ላይ የሆነ በመጨረሻው ዘመን ግን የባርያን መልክ ይዞ የተገለጠ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ስለ ኀጢአታችን ብዙ ልንፆም፣ በፀፀት ልናለቅስ፣ በርካታ ምፅዋት ልንሠጥና በድካም እስክንዝል ልንሰግድ እንችላለን ፡፡ ይህ ሁሉ ግን ይቅርታውን ደጅ የምንጠናበት መንገድ እንጂ በራሱ ፍፁም ሆኖ ይቅርታን የሚያስገኝ አይደለም፡፡ ይቅርታን ለማግኘት ለኃጢአታችን መስዋዕት ሆኖ የቀረበ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን ልንበላ ክቡር ደሙንም ልንጠጣ የግድ ያስፈልገናል፡፡

መጽሐፍ "ያለ ደም ሥርየት የለም" እንዲል ጌታም በቃሉ "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው፡፡ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም"፡፡ እንዲል ዕብ፣ዮሐ 653

ጸሎት- ቅዱስ አምላክ ሆይ አናመስግንሀለን፡፡ ከቸርነትህ ገናናነት የተነሣ ሥጋህንና ክቡር ደምህን ለህይወት ለመድኃኒት እንዲሆነኝ ሰጥተኸኛል፡፡ ይህም በሕይወት ዘመኔ የተቀበልኩት በዋጋ የማይተመን እኔን የመውደደህ ስጦታ ነው፡፡ ቸር ሰውን ወዳጅ ሆይ ወደ ሕይወት መድኃኒት እንዳልቀርብ ዲያብሎስ በብዙ የምክኒያት ሰንሰለቶች አስሮኛልና ፍታኝ፡፡ ምክንያትን ቆርጬ የምጥልበትን ኃይል አድለኝ፡፡ በእኔም ዘንድ መኖርያህን ታደርግ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን!አሜን!

አቡነ ዘበሰማያት



ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

 



Read more...

በዓለ ዕረፍቶሙ ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ ፭

‹‹ በዓለ ዕረፍቶሙ ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሐዋርያቲሁ ለክርስቶስ ወአእማዲሃ ለቤተክርስቲያን ››

ሐዋርያ ነጠላ ሲሆን ሐዋርያት ብዙ ቁጥርን ያመለክታል፡፡ ቃሉ ሖረ ከሚለው የግዕዝ ግስ የሚወጣ ሲሆን‹‹ተጓዥ›› ‹‹ሂያጅ›› የሚል ትርጉም ይሠጣል፡፡ የጌታ ሐዋርያት ይህ ስም የተሠጣቸው መልካሙን ዜና ይዘው ወደ ዓለም ሁሉ በመሄዳቸው ነው፡፡‹እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው….››እንዲል ማቴ 28÷19

ሐዋርያት እንደቃሉ ተጉዞው የዓለሙን መልክ ሁሉ ለወጡት፤ ጨለማውን ገፈፉት አልጫውን አጣፈጡት፡፡በምድር በአፀደ ሥጋ ከመኖራቸው ጀምሮ በስሙ ሞትን ተቀብለው ከዚህ ዓለም እስከመለየታቸው ባለው ጉዞ ብርሃንነታቸውን ገልጠው አሳዩ፡፡ጥንታዊት ሐዋርያዊትና ብሔራዊት የሆነችዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ (በሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ይሔው ትውፊት እንደተጠበቀ ነው) ከራሱ ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቃሉ የተማሩ የእጁን ተዐምራት ቆመው የተመለከቱ፤በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ ብዙ ምሥጢራትን የገለጠላቸው፤ በእጆቻቸው የዳሰሱት አብረውትም የበሉና የጠጡ፤ የመከራው የስቅለቱ፣የሞቱ፣የትንሳኤውና የዕርገቱ ቀዳሚ ምስክሮች፤ከራሱ ከባለቤቱም ሥልጣነ ክህነትንና የቤ/ክ አደራ የተቀበሉ በመሆናቸው ‹‹ሐዋርያ›› የሚለው መጠሪያ ከእነርሱ በቀር ለማንም ለማን ቀፅላ አታውቅም፡፡ ከእነርሱ በኋላ የተነሱትን ሁሉ የጠራቻቸውና የምትጠራቸው ሐዋርያነ አበው(Apostolic Fathers) የቤ/ክ ጠበቆች(Apologetics)፣ሊቃውንት፣አበውጳጳሳት፣መምህራን፣ካህናት ወዘተ… በማለት ነው፡፡ እኒህ ሁሉ የሐዋርያትን ሥልጣንና ተግባር ይዘው ቢገኙም ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለነበሩት የተለየ አክብሮት በመስጠት‹‹ሐዋርያ›› የሚለውን ስያሜ በእነሱ ላይ ብቻ ጠብቃው ኖራለች እንጂ ዛሬ ብዙ ደፋሮች እንደሚጠቀሙበት አይደለም፡፡ በነቢያትም እንዲሁ ነው፡፡

ስለ ሁሉ ሐዋርያት የሕይወት ገድል ለመተረክ ጊዜም አይበቃም አቅሜም አይፈቅድም፡፡ ነገር ግን ሐዋርያት ሁሉ ስለተወከሉባቸው ሁለቱ ታላላቅ ሐዋርያት ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በመጠኑ ማለት እወዳለሁ፡፡አንዱ የሕዝብ ሌላኛው የአሕዛብ ሐዋርያ ናቸውና፡፡ ከዚህ የወጣ የለም፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ከዓሣ አጥማጅነት ቅዱስ ጳውሎስ ከደማስቆ መንገድ እንዴት እንደተመረጡ፤የቅዱስ ጴጥሮስን የተለምዶ ሕይወትና ቅዱስ ጳውሎስ ምሁረ ኦሪትነት ለመተረክም አልሻም፡፡ ብዙዎቻችን የምናውቀው ነውና፡፡ ሁለቱም የተሠጣቸውን አደራ በትጋት ፈጽመው ናፍቆታቸው ተፈፅሞላቸዋል፡፡

ማንሳት የምፈልገው ከእነርሱ ሕይወት እኛ የምንማረው ምንድር ነው?የሚለውን ነው፡፡

 ሊቀ ሐዋርያትበዕድሜውም አዛውንት እንደመሆኑ ከጌታም ጋር ብዙ ጊዜ እንደማሳለፉም ቅድሚያ የቅዱስ ጴጥሮስን ሕይወት በጨረፍታ እንዳስሳለን፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹በዓሣ ፋንታ ሰውን የምታጠምድ አደርግሃለው›› ተብሎ ከተጠራበት ሰዓት አንስቶ ከጌታችን ጋር ማስመሰል በሌለበት ሕይወት ኖሯል፡፡ ከጌታችን የተሠወረ ምንም ነገር እንደሌለ የታወቀ ነገር ቢሆንም ቅሉ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ከራሱ በሚወጣ የዋህነትና ቅንነት በጎም ሆነ የሚነቀፍ ጠባዩ በጌታ ፊት የተገለጠ ነበር፡፡ በወንጌል የተፃፈው የቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት፤ ጥንካሬው ብቻ ሳይሆን ድክመቱ፣ስህተቱም ሆነ እውቀቱ፣ማስተዋሉም ሆነ ችኩልነቱ ብዙ ትምሀርት ትቶልን አልፏል፡፡ከጌታችን ጋር የነበረ ሕይወቱ በመውደቅና በመነሳት  የተሞረደየተቃናና የዳበረ ሐዋርያ ነው፡፡

ታላቁ ውድቀቱ ለታላቁ ትንሣኤው ምክንያት መሆኑን ማስተዋል ምን ያህል ያፅናናል፡፡ ምን ያህል ተስፋ መቁረጥን  ይሠብራል፡፡የቅዱስ ጴጥሮስ አዲስ ሕይወት ጅማሬ በጥብርያደስ ባህር ከጌታ ጋር ከነበረው ቆይታ ይነሳል፡፡ ‹‹የዮና ልጅ ስምኦን ትወደኛለህን?›› የምትለዋ ጥያቄ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት ወሳኝ ነበረች፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን ለታላቅ አገልግሎት ኃላፊነት ሊሠጠው ፈቃዱ ሆኗል፡፡ግን በእርሱ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል፡፡ እርሱም በሰጠው ምላሽ ፈተናውን አልፏል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ሦስት ጊዜ መካድና መፀፀት፤ የመድኃኒታችንም የይቅር ባይነቱ ስፋት ቅዱስ ጴጥሮስን ደግሞ ለተሻለ ሕይወት ወለደው፡፡ከውድቀቱ የተነሳ የተሻለ ጠንክሮ የተሻለ አስተውሎ የተሻለ ተቀርጾ ነበር የተነሳው፡፡ ዮሐ 21

የቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት በዚያች ቃል ታሠረች፡፡ ‹‹አንተ ሁሉን ታውቃለህ እንድወድህም አንተ ታውቃለህ›› በምትለዋ ቃል፡፡ ከዚያ ለጥቆ በነበረ ሕይወቱ መልሱ ይኸው ነበር፡፡ ስለምን ትሰብካለህ?ስለምን ትፀልያለህ?ስለምን ታመሠግናለህ? ስለምን ትታሠራለህ?ስለምን ትገረፋለህ?ስለምን ትሞታለህ? ስለምንስ ትኖራለህ?ወዘተ… ብለን ብንጠይቀው መልሱ ምክንያቱም ‹‹ስለምወደው››  የሚል ነው፡፡ በአንተስ ላይ ስለምን ይህ ሁሉ ይደርስብሃል ብንለው ‹‹ለእርሱ ባለኝ ፍቅር ላይ እርግጠኛ ስለሆነ›› የሚል መልስ ይሰጠናል፡፡

ጌታችን ሐዋርያቱን በቃሉ ላይ የሾማቸውና ትምህርታቸውን በብዙ ድንቅ ተዓምራት ያፀና የነበረ እንዲሁ አይደለም፡፡ወደ እስራት፣ወደ ግርፋት፣ ወደ መከራ፣ ወደ ሞት፣ የወሰዳቸውም ለእርሱ ባላቸው ፍቅር እርግጠኛ ስለሆነ ነው፡፡ እኛስ ጋር ያለው እንዴት ነው?

ጸሎታችን፣ምስጋናችን፣ጾማችን፣ምጽዋታችን … ወዘተ አጠቃላይ ክርስቲያናዊ ሕይወት የምንኖረው ለምንድነው? አገልጋዮችስ የምንቀድሰው፣ ሕፃናትን የምናጠምቀው፣ በሰዓታት በማኅሌት የምናድረው፣ የምንሰብከው ወዘተ… ለምንድር ነው? በዚህ ሁሉ እኛ ለክርስቶስ ያለንን ፍቅር እገልጣለን ወይስ የልማድ እስረኞች ነን፡፡


 

የአንድ ሰነድ ማረጋገጫው ማኅተም እንደሆነ ሁሉ እኛም ከክርስቶስ ጋር ላለን ሕብረት አብረነውም የምንሠራ ለመሆናችን ማኅተሙ ‹‹ትወደኛለህን?›› ብሎ ለሚጠይቀን ጥያቄ የምንሰጠው መልስ ነው፡፡ ይህን ማሰብ ልብን ያሳምማል፡፡ሁሉን በሚያውቀው በእርሱ ፊት መተወን ሲያስተውሉት ያሳቅቃል፡፡ ተውኔታችንን ሕይወት አልባ ትወናችንንም ለዛ ቢስ ያደርገዋል፡፡ እንዴት ያለ አለመታደል ነው የሕይወት ዘመን ክስረት?!

ዛሬ ያለን የክርስቶስ ተከታዮች ሕይወታችን ለሌላው ትምህርት መሆንም አልቻለም፡፡ምክንያቱም ሁል ጊዜ የሚገለጠው ጥንካሬያችን ንፅሕናችን ቅድስናችን እንጂ ድክመታችን ጥፋታችን ነውራችን አይደለምና፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ  ‹‹አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› ብሎ እምነቱ እንደተገለጠ ‹‹የምትሉትን አላውቀውም››ብሎ የተናገረው ክህደቱም ተገልጾ በመታየቱ ከሕይወቱ ተማርን፡፡ ሁሌ ጥንካሬን ሁሌ ቅድስናን የምንሰማበትን ሕይወት ግን ከምንማርበት ይልቅ ተጠራጠርነው፡፡

በቤተ/ክ ታሪክ ለታላቅ ቅድስና ሕይወት የበቁ ቅዱሳን በቀደመ ሕይወታቸው ታላላቅ ስህተት የሠሩ ናቸው፡፡በእነርሱ ላይ የተገለጠች ታላቅ የእግዚአብሔርን ይቅርታ በማድነቅ ለንስሐና ለቅድስና ሕይወት እንድንበረታታ ነው ታሪካቸው የሚተረከው፡፡

ለእግዚአብሔር ባለን ፍቅር እርግጠኞች ከሆንን በስሕተት ወይም በፍርሃት ለሚገጥመን ውድቀት ይቅርታው ቅርብ ናት፡፡ ከወደቅንም በኋላ ማረጋገጥ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ለንስሐ አይቀርብም፡፡ ፍቅር የሌለው ንስሐም ሥርየትን አያስገኝም፡፡ከፍፁም ፍቅር የተነሳ ንስሐ ስንገባ ግን የጌታ እግዚአብሔር ይቅርታው በእኛ ላይ ትደንቃለች፡፡ ለእንዲህ ዓይነት ንስሐ የጌታ እግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ቀደመ ክብራችን መመለስ ብቻ አይደለም ከዚያ ወደሚበልጥ ከፍታ በማውጣት ትገለጣለች፡፡

በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ጌታ እግዚአብሔርን በስንቱ ነገር ይቅርታ እንደምንጠይቅ ግራ እስኪገባን ድረስ በደላችን ይከድነናል አለማስተዋላችንም ይሸፍነናል፡፡የሚታገሉንን ለመጣል፣የሚቃወሙንን ለማጥፋት፣የሚያጠቁንን ለማጥቃት ስንት ጊዜ ተጠበብን፡፡ስንቱን ሸፍጥ በስሙ ስንቱን በደል በኃይሉ የተገኘ ፍትሕ አስመሰልነው፡፡በፍቅር ሳንታገል ተሸንፈን ሳናሸንፍ የትግላችን መሪ የውጊያችን ፊታውራሪ ልዑሉ መሆኑን ለፈፍን፡፡ የጥላቻችንን ድል የቅዱስ ስሙ መመስገኛ አደረግን፡፡ ታዲያ ለዚህ ላልተገለጠው በደላችን የሸፍጥ ጽድቃችን እንደ ነቀርሳ ውስጥ ውስጡን ርኩሰት ለበላው ቅድስናችን ቀርቶ ለተገለጠው ኃጢአታችን ምን ንስሐ ይበቃዋል? አሁን የኖርነውን ዕድሜ ደግሞ ቢጨመርልን ለመፀፀት አይደለም ለማስታወስ እንኳ ይበቃን ይሆን?

በሁሉ የምመስልህ ወንድሜ ሆይ! በሕይወት ለመቆየታችን በፊቱም ለመታየታችን የኃጢአትን ይቅርታ ለማግኘታችን ምክንያቱ የልዑሉ የይቅርታ ስፋት እንጂ የእኛ የንስሐ ጥልቀት አይደለም፡፡ ይህን ባመንበት ቅፅበት ወደ ምህረት ደጃፍ መቅረብ እንጀምራለን፡፡

ግን ደግሞ እንደ እውነቱ የሁላችን ኃጢአት ተገልጦ አለመታወቁ የይቅርታ ልብ በጠፋበት በዚህ ዘመን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሰውን ፀፀቱን ንስሐውን አይቶ ይቅር (ከልቡ) ብሎ የተሻለ ክብር ከሚሠጠው ይልቅ የሚረግም የሚፈርድና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደባ በበዛበት ጊዜ ተጋላጭ ሆኖ መገኘት አለመፈለጉ በዘመኑ ክርስቲያኖች ላይ ያለንን የእምነት ጥርጣሬ የሚያሳይ ነው፡፡ ማስተዋል አቃተን እንጂ የክርስትና መሠረቷ ይቅርታ ነበር፡፡ ጌታችን በመስቀሉ ደሙን አፍስሶ እኛ በበደልን እርሱ ክሶ ይቅር ባይለን ኖሮ ወዴት እንታይ ዘንድ አለን ነበር? እርሱም ያስተማረን የሰማዩ አባታችሁ ይቅር እንዲላችሁ እናንተም የበደሏችሁን እንዲሁ ይቅር በሉ በማለት ነበር፡፡ሰው ራሱን የሚገልጠው ውጤቱን ገምቶ ነው፡፡ የይቅርታ ጉልበት በመካከላችን ተገልጦ ቢሆን ኖሮ የማስመሰል ሕይወት ምንኛ በሞተ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ይቅርታ ስትደክም ኃጢአት በሥውርነገሠች፡፡

ከቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት በጨረፍታ ቢሆንም እንኳ ከቀመስን የአሕዛብ ሐዋርያ ወደ ተባለ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እናልፋለን፡፡

አስቀድሜ ይህን ለመጻፍ በመድፈሬ በራሱ ታላቅ ይቅርታን ሕይወታቸውን ኖረውለት ሞቱን በሚመስል ሞት ከመሰሉት ከሐዋርያት ጌታ እለምናለሁ፡፡የዚህ የተወደደ ሐዋርያ ሕይወትስ ይጽፍ ዘንድ ማን ይደፍራል? ይህ ከመታሰብ በላይ ነውና፡፡ እንዲያው ለቅምሻ ያህል እንሞክራለን፡፡በዚህ ጽሑፍ ተነሣስታችሁ ይበልጥ ቅዱስ ጳውሎስን ማወቅ ለምትፈልጉ ግንየሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሰባት ቁጥር ስድሳን መነሻ አድርጋችሁ የሐዋርያት ሥራን ሙሉውንና መልእክታቱን አንብቡ፡፡ስታነቡ ግን በጸሎትና በታላቅ ተመስጦ ይሁን፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ ቃልና ዓረፍተ ነገር የውቅያኖስ ያህል ጥልቀት ያለው ነውና፡፡

ቅዱስ ጳውሎስን በመጽሐፍ ቅዱስ የምንተዋወቀው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲገደል የገዳዮቹን ልብስ ሲጠብቅ ነው፡፡ ምንም እንኳ የታላቁን ሰማዕት ደም ለማፍሰስ እጆቹ ድንጋይ እንዳያነሱ መንፈስ ቅዱስ ቢጠብቀውም በመገደሉ ግን ተስማምቶ ነበር፡፡የወደፊቱን የአሕዛብ ቤ/ክ ካህንና ሐዋርያ መንፈስ ቅዱስ ከደም ጠብቆታል፡፡ የሰማዕታት ደም ሥራ ሳይሠራ በከንቱ አይቀርምና የቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ጳውሎስን ለቤ/ክ አስገኝቷል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ለኦሪት በነበረው ቅንዓት ክርስቲያኖችን ለማሰር ከሊቀ ካህናቱ ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ነው ከክርስቶስ ጋር የተገናኘው፡፡ ከኦሪት ሊቀ ካህናት ሰዎችን ለማሠርና ለማሠቃየት ነፃነታቸውን ለመግፈፍና እምነታቸውን ለማስካድ ሥልጣን ተቀበለ፤ ከአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ከጣዖት፣ከኃጢአት፣ ከድንቁርና ጨለማና ከዲያብሎስ እስራት ነፃ እንዲያወጣ፤በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለሚገኝ አዲስ ሕይወት በእምነት እንዲፀኑ ለማስተማር ሥልጣን ተቀበለ፡፡የኦሪቱ ሊቀ ካህናት በቁጣና በጭካኔ ላከው የአዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህናት ግን በፍቅርና በርኅራኄ አሠማራው፡፡

ጌታ እግዚኣብሔር ያለ ዓላማሰውንም ሆነ ሌላውን ፍጥረት አልፈጠረምና ዓላማ ያለው ሰው ይወዳል፡፡በእርግጥ ሰዎች አጥፊ መሆኑን አምነው የሚይዙት ዓላማ ያለውን ያህል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ካለ ማስተዋል የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚዋጉ እየመሰላቸው እራሱን እግዚአብሔርን የሚያሳድዱ አይጠፉም፡፡ጌታም በቃሉ‹‹…የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል›› ያለ ይህን ሲያመለክት ነው፡፡ ዮሐ16÷2

ነገር ግን ሁልጊዜ ክፉ ነገሮችን ለበጎ የሚለውጥ ጌታ እግዚአብሔር የቅዱስ ጳውሎስንም ቅንዓት ለወንጌል አገልግሎት ለቤ/ክ መስፋት እንዲልውል ፈቃዱ ሆነ፡፡ የዮሴፍ ወንድሞች ቅንዓት በኋላ ለእስራኤል ከረሃብ መዳን ምክንያት እንደሆነ የቅዱስ ጳውሎስም ቅንዓት አሕዛብን ከቃለ እግዚአብሔር ረሃብ ለመዳን ምክንያት ሆኗል፡፡


 

በደማስቆ መንገድ ቅዱስ ጳውሎስ የጠየቀው ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ነው፡፡ የመጀመሪያው ጌታ‹‹ስለምን ታሳድደኛለህ?››ሲለው፤‹‹ጌታ ሆይ አንተ ማነህ?›› በማለት የጠየቀውና ማንነቱን ካወቀ በኋላ ደግሞ ‹‹ጌታ ሆይ ምድ አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?›› የሚለው ፍፁም ራስን የመስጠት(የመገዛት)ጥያቄ ናቸው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ የሚያናግረው የሚወቅሰው ማን መሆኑን ካወቀና ምን ማድረግ እንዳለበት ከተናገረው በኋላ ወደ ኋላ አልተመለሰም፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባው እንድትነግረው የተላከውም ወደ ቤተክርስቲያን ነው፡፡

ፊት ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ምዕመናንንም ለመሳደድ ተሰልፎ እንዳልነበር ኋላ ግን ጣዖትንና ክህደትና የሚያፈርስ የመንፈስ ቅዱስ መዶሻ፤የጠንቋና የአስማተኞች ሥራይ ማርከሻ፣የሕሙማንና ተስፋ የቆረጡ ሁሉ መፈወሻ ሆነ፡፡ ይህ ነው ለውጥ፤ ይህ ነው ክርስትና፤ ይህ ነው ሐዋርያነት፡፡ 

ዛሬስ ክርስቶስ ከመሳደድ አርፏልን? የሚሳደደውስኢ-ክርስቱን በሆኑት ብቻ ነውን? በሚሉት መጠይቆች እስኪ ራሳችንን እንመርምር፡፡

ኢ-ክርስቱን በሆኑት ክርስቶስ እንደሚሳደድና እንደሚታረድ በሶርያ በኢራቅና በሊብያ ያየናቸው የዘመናችን ዘግናኝ ጭካኔዎችና ቁርጥ የሰማዕትነት መንፈስ በቂ ማስረጃ ስለሆነ ብዙ ማለት አያስፈልግም፡፡(በረከታቸው ይደርብን)

በእኛ በክርስቲያኖችስ ክርስቶስ አይሳደድም? ባል ሚስቱን፤ሚስት ባሏን፤ወላጆች ልጆቻቸውን፤ልጆች ወላጆቻቸውን፤  ወንድም ወንድሙን፤እህት እህቷን ፤ ጓደኛ ጓደኛውን፤ ጎረቤትም አብሮት የሚኖረውን፣የትምህርት የሥራ አጋሩን ወዘተ… ቀን ስጠኝ ጊዜ ፈቀደልኝ ብሎ የሚበድል የሚያሰቃይ ላቡን ድካሙን የሚቀማ ከሥራ የሚያፈናቅል ይህ ሁሉ ክርስቶስን አሳዳጅ አይደለምን?

በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ (በቤተመንግስትም ሆነ በቤተክህነት) የሥልጣን ዙፋን ላይየተቀመጥን ጊዜ ሰጠን የብዕርናየአፈሙዝ ኃይል አጋደለልን ብለን ድሀውን የምንረግጥ፤ ያለመማለጃ ጆሯችን የማይሰማ ዓይናችን የማይገለጥ፤ ስህተታችንን የሚያርም ግፋችንን የሚቃወም ሲገኝ የምናስር የምናግዝ የምናሠቃይ የምንገድል ክርስቶስን ማሳደድ አይደለምን?

ዛሬ በእኛ ክፋት ክርስቶስ በረሃብ ጠውልጓል፤ የጎዳና አዳሪ ሆኗል፡፡ በመድኃኒት ከሰው ተራ ወጥቶ ይባዝናል፤ በጠበል በሆስፒታል ጓሮ ወድቋል፡፡ እኛ ግንከረሃቡ ነጥቀን ታላላቅ ቤተ መቅደሶች እናንጻለን፤ ጥም ካደረቀው ሰውነቱ ለተቀዳ ደሙ የወርቅ ጽዋ እንገዛለን፤እርሱ ጎዳና ወድቆ እኛ በምንጣፍ እናስቀድሳለን፤ የእርሱ እርቃን ተጋልጦ እኛ መጋረጃ እንመርጣለን ፡፡

የጥፋት ሀብት የሰበሰብን ረሃብ ክብሯን ያስጣላት ማጣት በሴትነቷ የፈተናት እህታችንን ርኩሰታችን ልንተፋባት ብልግናችንን ልናስታግስባት በገንዘብ ስናማልላት ከሰውነት ክብር አዋርደን ለመናገር የሚቀፉ ነውር ስንፈፅምባት ክርስቶስን ማሳደድ መሆኑን ረሳነውን?ለመዘርዘር የማይበቃን በታናናሾች ላይ የሚደረግ ሁሉ በእርሱ ላይ እንደሚደረግ ለነገረን ለእርሱ ይህ ሁሉ ስደቱ ሕመሙ አይደለምን?

የሰውን አእምሮ አፍዝዞ ሕዋሳቱን አደንዝዞ ለሀገር ለወገን በሚጠቅምበት የወጣትነት ዕድሜው የእፅ ምርኮኛ የሱስ እስረኛ በማድረግ ከዚያ በሚገኝ ገቢ ኑሮአቸውን ያጸደቁ ‹‹ቢዝነስ›› ነው እያሉ የሚመጻደቁ እኒህ ሁሉ ክርሰቶስን አሳዳጆች አይደሉምን?

ዛሬ የዓለምሕዝብ ምን ያህሉ ይሆን በዚህ ሥራ የተጠመደ? ብዙዎቻችን አገር አቋራጭ ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን ፣የኬሚካልና ባዮሎጂካል መሣሪያዎችን ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች እያልን ስንቃወም እንኖራለን፡፡ ነገር ግን ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲዎችን፣ ልቅ የተለቀቁ ጎጂ መጤ ባህሎችን፣ ሰው ፈሪሃ እግዘአብሔር እንዳይኖረውና በራሱ ላይ ብቻ ተጣብቆ እንዲኖር የሚያስተምሩ ሙት የፍልስፍና መጻሕፍትን፤በፊልም፣በሬድዮ፣በኢንተርኔት የሚለቀቁ ልቅ የወሲብና የወንጀል ፊልሞችና ፕሮግራሞችን ወዘተ… እኒህ ሁሉትውልድ ጨራሽ መሣሪያዎች  የሚያሳስቡት ግን እጅግ ጥቂቶችን ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብሎ በጠየቀው ጥያቄ ታላቅ መልስ አግኝቷል፡፡

የጌታችን መልስ‹‹አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ›› የሚል ነበር፡፡ በዚህ መልስ ጌታችን ለቅዱስ ጳውሎስ የምዕመናን ስደት የእርሱ ስደት፤የክርስቲያኖች መከራና ስቃይ የእርሱ መከራና ስቃይ መሆኑን አስረድቶታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለተበደሉ የሚፈርድላቸው ለተገፉ የሚበቀልላቸው፤ ትዕቢተኞችን የሚያዋርድ የተዋረዱትን ደግሞ ክብር የሚሠጥ፤ የአቤልም ሆነ የቃየል አምላክ ሥራቸውንም የሚመዝንና ዋጋቸውን የሚከፍል በባህርዩ የማይሞት ሥልጣኑ የማይሻር ለግዛቱም ወሰን የሌለው የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ መሆኑን ከመልሱ ተረድቷል፡፡‹‹የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሃል›› የሚለው ማስጠንቀቂያ አጥንቱ ደርሶ ዘልቆ ሳውልን አርዶታል፡፡ዛሬም በመውጊያው ብረት ላይ የሚዘብት ብዙ አለ እስኪያዝ ድረስ፡፡

ወዳጄ! በየትኛውም የሥልጣን ወንበር ብትቀመጥ፣ የሀብት ጫፍ ብትቆናጠጥ የዕውቀትን ማማ ብትረግጥ የሁሉ መጨረሻ አንድ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ለሥጋ እርካታ ይሆን እንደሁ እንጂ ነፍስህን ከተጠያቂነት አያስጥላትም፡፡


 

የዛሬን አያድርገውና ታላቅ የክርስቲያኖች መናገሻ የነበረችው አግያ ሶፍያን የመሰለ ታላቅ ቤተክርስቲያን የነበረባት ቁስጥንጥንያ የዛሬዋ ኢስታንቡል የሮማ ግዛት ሁለተኛዋ መናገሻ ነበረች፡፡ በአንድ ወቅት በግርማው የተፈራ በዝናው የከበረ በኋይሉ የታፈረ ታላቅ ቄሣር ዘውድ ጫነ፡፡ በዚህ በዓለ ንግስ ላይ መኳንንቱና መሳፍንቱ እንደየማዕረጋቸው ንግግር እያደረጉ ታማኝነታቸውን ይገልጡ ነበር፡፡ቤተክርስቲያንን በመወከል በጊዜው የነበረው ፓትሪያርክ ንግግር እንዲያደርግ ሲጋበዝ በዙፋኑ ላይ በታላቅ ግርማ ተቀምጦ ለነበረው ቄሣር እንዲህ አለ‹‹የዓለምን የሥልጣን ጫፍ ጨብጠሃል፤ መግደልም ሆነ ማዳን የሚችል ሰይፍ ታጥቀሃል፤ ካንተ በታች እንጂ ካንተ በላይ የሚታይ የለም፤ሁሉን ማድረግ እንደምትችል አንተ ታምናለህ እኛም ይመስለናል፤ግን ይህ ሁሉ እውነት ያይደለ ቅዠት ነው፡፡ምክንያቱም ያመንካቸው የሚክዱበት ወዳጆችህ የሚሸምቁበት ሰይፍ የጨበጠ ክንድህ የሚዝልበት ከሁሉ በላይ በሆንክባት ምድር ከሥሯ ተኝተህ ሁሉ ከበላይህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህ!››

ማመናችን ወይም አለማመናችን የማይለውጠው የዘላለም እውነት ከፊታችን ይጠብቀናል፡፡ ከዚያ እውነት ጋር የምንገናኝበት ቅጽበት ለእያንዳንዳቸን ከጥላችን ይልቅ ቅርብ ነው፡፡በየትኛውም ቀንና ሰዓት ደቂቃና ሰኮንድ ያን እውነት በድንገት እንጋፈጠዋለን፤እጃችንን እንዘረጋለን ወደ ሚወደውም ይወስደናል፡፡ይኸውም‹‹ሞት››ነው፡፡ ልክ በዚያች ቅፅበት እንኳን በሌላው ላይ በራሳችን ላይ ያለን ሥልጣን ያበቃል፡፡በምድር ሳለን የተሠጠን ዕድል ለሞት መዘጋጀት እንጂ ሞትን ማስቀረት የሚችል አይደለም፡፡ከሞት ማዶ ከመቃብርም ወዲያ በዳይና ተበዳይን ገፊና ተገፊን ለመዳኘት ሥልጣን ያለው እውነትና ፍትህ የዙፋኑ ጌጥ የሆኑ‹‹የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ›› ያለው እርሱ ሁሉን ይጠብቃል፡፡ በዘላለማዊው ዳኛ ፊት በኃፍረት ወይም በሀሴት ለመቆም ውሳኔው ያለው በእጃችንየተሠጠንም ጊዜ አሁን ነው፡፡መለወጥ ከፈለግን መለወጥ ትችላለንና ይህተጽፎልናል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ከሰማና የሆነበትን ካየ በኋላ ለመወሰን ያለው ጊዜ አሁንመሆኑን አውቋል ፡፡ኅሊናውን ማንበብ ቢከብድም ደግሞ ከጠየቀው ጥያቄ ቀድሞ የኖረበት እውነት መናዱንና አዲስ ለተገለጠበት እውነት ራሱን ምርኮ ለማድረግ መዘጋጀቱን ያሳያል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን የለመደውን፤ረጅም ዕድሜ የኖረበትን፤ እውነት ነው ብሎ የተቀበለውን በቀላሉ መላቀቅ ይከብደዋል፡፡መክበድ ብቻ ሳይሆን ያስፈራዋል፡፡እንደ ታላቅ ሽንፈት ስለሚያየው እልህ ይጋባል፡፡ወደ ሕይወት መንገድ ለመምጣት የብዙዎች ችግር ይኸው ነው፡፡

ይልቁንም አንድ ቀን ከጌታ እግዚአብሔር ጋር የሚኖረን ግንኙነት (የተለየመገለጥ) በራዕይ፣ በሕልም፣ በተዐምራት፣ በመከራ፣ በፈተና፣ በሞት… ወዘተ ሊሆን ይችላል ይዘነው የነበርነውን እውነት ይበልጥ ያጎላልናል ወይም የተከበርክበት እውቀት የደሰኮርከው ፍልሰፍና የሰበከው ስብከት የሞትክለት ሕይወት ባዶ መሆኑን ያሳይሃል፡፡

እውነት በባሕርይዋ እንደ እሳተ ገሞራ ያንቀላፋች ፍም ናት፡፡ጭምትነት፣ ገርነት፣ ራስን መሰወር፣በሒደት በመድመቅና ኃይሏን በመግለጥ፣ በዘመናት ውስጥ ሳትፋለስ ፀንታ በመቆየትም ትታወቃለች፡፡ ጊዜን መስላ አትገለጥም፡፡ጊዜያት ሁሉ የእርሷን መገለጥ አብሳሪ ታሪኳንም ዘካሪ ይሆናሉ እንጂ፡፡ አዝማናትን በመለወጥ እንጂ በመመሳሰል አትታወቅም፡፡ሁሉን ትማርካለች ሁሉን ትስባለች ለሁሉ ራሷን ትሰጣለች፡፡

ያወቋት በድካም ውስጥ ኃይልን፣በድንቁርና ውስጥ ጥበብን፣ በንድየት ውስጥ ብልጥግናን፣ በሞት ውስጥ ሕይወትን ያመልካሉ፡፡ ጠቢባንና አስተዋይ ነን ከሚሉ ተሰውራ ለሕጻናትና ለዚህ ዓለም ሞኞች የመገለጧ ምሥጢርም ይኸው ነው፡፡ ምርጫ እንጂ ሽርክና የእርሷ ፈሊጥ አይደለም፡፡ እርሷን የሚሹ ሁሉን ያጣሉ ከእርሷ የሚሸሹም የሚበልጠውን ያጣሉ፡፡ ያቺ ቀን ከባድ ናት የኖርክበት ሲናድ ሕይወትህን የሰጠህለት መና ሲሆን የምታይባት ቀን፡፡ያቺ ዓለም የዚህን ዓለም ሸቀጥ ሊያሳርፍ የሚችል ወደብ የላትም፤ቀድሞ ከዚያው የተሠጠህንና አክብረህ የያዝከውን ይዞ ከመሔድ በቀር፡፡

ጳውሎስ ተማረከ! ኃይሉ፣እውቀቱ፣ስሜቱ፣ ፍላጎቱ፣ የመኖር ዓላማው ወዘተ… ተማረከ፡፡‹‹ጌታ ሆይ ምን አደረግ ዘንድ ትወዳለህ?›› በሚል የእውነት መንፈስ ራሱን እስከወዲያኛው ሰጠ፡፡ የእርሱን ምኞት ቀብሮ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ኖረ፡፡ የዳግም                  ልደቱየሕይወት ፍልስፍና ‹‹ብንኖር ለክርስቶስ እንኖራን ብንሞትም ለክርስቶስ እንሞታለን›› የሚል ነበር፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ሰውን በሁለት መንገድ ይማርካል፡፡ የመጀመሪያው በፍቅሩ ይማርካል፤በቃሉ ይጠራል በቸርነቱ በርኅራኄው ይጎበኛል፡፡ ሰምተው የመለሱለት ሕይወትን ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛው በኃይሉ በሥልጣኑ ይማርካል፡፡ ይህ ለሕይወት የሚሆንላቸው እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ግን ፍርድ የሚያገኛቸው ናቸው፡፡

ካለፈው የሕይወት ውጣ ውረድ ልምዳችን በመነሣት የጌታ እግዚአብሔርን ከኅሊና በላይ የሆነ ገናንነት በመረዳት ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ምርኮ አድርገን ብንሰጥ ሰማይና ምድር የሚዘክሩትን ሥራ በእኛ ይሠራል፡፡ስማችንም በሰማያዊው መቅደስ በሕይወት መጽሐፍ ይፃፋል፡፡በሕያዋን ምድር በበጉ ከተማ እንግዶችና መጻተኞች አንሆንም፡፡ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነንና፡፡


 

ከሁለቱ የቤተክርስቲያን አዕናቁ ሕይወት በላዕላይ ዳሰሳ ይህን ከተማርን ከዘመኑ አንጻር አገልጋዩች ምን ሆነው (ታጥቀው) መገኘት ይኖርባቸዋል የሚለውን በጥቂቱ እንመልከት፡፡

1.  በመንፈሳዊውም ሆነ በዘመናዊው እወቀት ሙሉ ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡በመንፈሳዊው የቤተክርስቲያንን እውነተኛ አስተምህሮ በተጨማሪም የተቃዋሚዎችን አካሔድና አስተምህሮ ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በየዘመናቱ የተነሱ የሰው ልጅን አስተሳሰብ ያጣመሙ ወይም ያቃኑ ፍልስፍናዎችን መረዳትና በቂ መልስ(ሙግት) ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡በሳይንሱም በይበልጥ ከሰው ልጆች ሕይወት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለቸው በሕክምና፣በሥነ-ልቦና፣በማኅበራዊ ሳይንስ፣ ኪነጥበብ፣ ቴክኖሎጂ ወዘተ… ጋር ትውውቅ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ዛሬ የሰውን ጥያቄ ጹም ጸልይ በሚል ብቻ የምንመልስበት ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡ በክርስቲያኑ በእምነት የሚገለጡና በአመክንዮ የሚመለሱትን ለይተን ማሳወቅ ከእኛ ይጠበቃል፡፡

ምዕመናንም መንቃት ከልማድ መውጣት ይጠበቅብናል፡፡ ብዙዎቻችን ለቤተክርስቲያን ከጧፍ፣ከዕጣን ፣ከመጋረጃና ከምንጣፍ የዘለለ መባመስጠት አለመደብንም፡፡ ስንቶቻችን ለቤተክርስቲያን አገልጋዮች በይበልጥ መንጋውን ለመጠበቅ ለሚደክሙ መጻሕፍትን፣ የትምህርት ዕድሎችን፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣በጽሙና ሊያነቡ የሚችሉበትን ሥፍራ፣ እነርሱ ያለ ሀሳብ የቤተክርስቲያንን ሥራ እንዲሠሩ ለኑሮ የሚስፈልጋቸውን ወጪ፣ የመጻሐፍት የመጽሔትና የጋዜጣ ማዘጋጃ ወጪን የመሳሰሉት ስናመቻችና ስንደግፍ እንታያለን፡፡እኛ ብል ለሚበላው ምንጣፍ ስንጨነቅ ስንቶችን የኃጢአትና የክህደት ብል እንዳይበላቸውየሚጠብቅ እውቀት በከንቱ እየቀረ ነው፡፡በተጠናና  በተቀናጀ ስልት በሚዘረጋ የትምህርተ ወንጌል አደረጃጀት እንጂ በሠርክ ጉባዔ ስብከትና በበዓላት ድምቀት ብቻ ትውልዱን ይዘን እንቀጥላልን ማለት ከሞኝነት ያለፈ ዕብደት ነው፡፡ በተናጠልም ሆነ በኅበረት በመሆን አሥራት በማውጣት ወይም የተለየ በጀት በመመደብ አገልጋዮችን መደገፍ ከሚበልጠውየወንጌል ትሩፋት መሳተፍ ነው፡፡ የጥንቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምዕመናን መለያ የአብነት ተማሪዎችንና መምህራንን መደገፍ መጻሕፍትን አጽፈው አስደጉሰው ለየአድባራቱና ገዳማቱ መስጠት ነበር፡፡

2.  የለውጥ አላማጆች(Activist) መሆን፡- በዓለም ታሪክ በተደረጉ የለውጥ ጉዞዎች፣የነጻነት ትግሎችና፣የሰው ልጆች ድኅንነት መጠበቅ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ድርሻ ጉልህ ነበር፡፡ማሀተማ ጋንዲ፣ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ አቡነ ዴዝሞን ቱቱ፣ በሀገራችን ታሪክ ስንመጣ መንግሥታትን በማደራርና ደም መፋሰስን በማስቀረት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት፣የሃገርን ነጻነት በማስጠበቅ ጻድቁ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና የጎሬው አቡነ ሚካኤል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ዛሬም ካለን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በሰው ልጆች ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቶች መከበር፣በተፈጥሮ ደኅንነት ጥበቃ፤በሀገራዊና ማኅበረሰባዊ  ጉዳዮች ቀዳሚ ወኪሎችና ተሟጋቾች መሆን ይጠበቅብናል፡፡በዘመናዊው አስተሳሰብ የፈላስፎች የፖለቲከኞችና የኪነ-ጥበብ ሰዎች ትልቁ ግብ ሕብረተሰቡን ከሃይማኖትና ከሃይማኖት አባቶች ምሪት ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖቱን የሚያጠብቅና የሃይማኖት አባቶቹን የሚያከብርና የሚከተልን ሕዝብ እንደፈለጉ መንዳት አይቻልምና፡፡ ሃይማኖትና የሃይማኖት አባቶች ለብዙ ሺህ ዓመታት ይዘውት የነበረውን ቦታ ፈላስፎች ፖለቲከኞችና የኪነ-ጥበብ ሰዎች መቆናጠጥ ይፈልጋሉ፡፡በምዕራቡ ዓለም የሆነውና በስኬት የተፈፀመው ይኸው ነው ፡፡ ሕብረተሰቡ በስልጣኔ ስም ላመነበት ሳይሆን ለተቀረፁለት ሥርዓት(system)ባርያ ሆኖ እየኖረ ያለው ለዚህ ነው፡፡በንግግር የሚጠቅሳቸው በኑሮ ዘይቤውም አብነት የሚያደርጋቸው እነዚህኑ ስለሆነ ከፍተኛ ለሆነ የሥነ-ምግባር ዝቅጠትና የሞራል ውድቀት ተደርጓል፡፡ሌላው ቀርቶ ከሰብአዊ ባህርይ እስከማፈንገጥ ደርሷል፡፡ምክንያቱ አርአያ(Icon) ከሚላቸው የሚያየውና የሚሠማው ቅንጦትን፣ ስግብግብነትን፣ዝሙትን፣ሰዶማዊነትን ወዘተ…ነው፡፡ይህ በእኛ እንዳይደገም ተጨባጭና ቀጥተኛ(Rational)በሆነ መንገድ የሚመክሩ የሚሞግቱና ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በሕዝቡ የታመኑ የሃይማኖት አባቶች መሆን ይጠበቅብናል፡፡

ወደድንም ጠላንም በሕዝቡ ውስጥ ያለንን ቦታለመንጠቅ ያሰፈሰፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተወሰነ ደረጃ እየተሳካላቸውም ነው፡፡ ለመመለስ ግን አሁንም አቅሙ አለን፡፡ሕዝቡ የሚፈልገው በእኛ እርግጠኛ መሆንን ብቻ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ልንሠጠው ያልቻልነው ያን ነው፡፡በየትኛውም ዘርፍ ሕዝቡ ከኋላ ሆኖ የሚገፋው ሳይሆን ከፊት ሆኖ የሚመራው፣ለዓላማው እንዲሞት የሚሰብከው ሳይሆን ሞትን ተጋፍጦ የሚያሳየው መሪ ይፈልጋል፡፡ለዚህ ደግሞ ከመንፈሳዊ መሪዎች የቀረበ የለም፡፡

በበጎ አድራጎት ሥራ ቤተክርስቲያንና የሃይማኖት አባቶች ፊትአውራሪ መሆን ሲጠበቅብን ከእኛ ይልቅ እየተሠራ ያለው በጎ ኅሊና በቀሰቀሰላቸው ሰው መሆን ግድ ባላቸው ምዕመናን ነው፡፡መቅደም ሲገባን ተቀድመናል፣ እንኳ ለመምራት ለመመራትም በምናስቸግርበት ሁኔታ ላይ መገኘታችን ምንኛ አሳዛኝ ነው፡፡

ሕዝቡ ግን አሁንም ከሃይማኖት አባቶች ጉያ ላለመውጣት ያለው ምኞት ትንሽ በሚንቀሳቀሱ አባቶች(እውነተኞች ወይም አስመሳዮች)ሥር ከሚያሳየው ተስፋን ያዘለ መሰባሰብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ልንሠራ ነገሮችን ልንለውጥ የምንችልበት ቀን ሳይጨልም መንቃት የእኛ ፋንታ ነው፡፡


 

3.  ጽናት፡- ኅብረተሰቡ በተለያየ ችግር ምክንያት ቅስሙ ተሰብሯል፡፡የኢኮኖሚ ቀውስ፣ሥራ አጥነት፣ጦርነት፣ ያልተገለጠ የየማጀቱ ረሃብ ወዘተ… አድቅቆታል፡፡ከዚህ ሁሉ መጽናኛው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡እግዚአብሔርን እንዳገኘ የሚሰማው ደግሞ የሃይማኖት አባቶቹን ሲያገኝ ነው፡፡

በመሆኑም አገልጋዮች ከችግር ይልቅ መፍትሔ ላይ የሚያተኩሩ ለየትኛውም አስጨናቂ ሁኔታ የማይበገሩ መንፈስ ጽኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ምድር የሥነ-ልቦና አማካሪዎች አይታወቁም፡፡ አሁን እንኳ በተለያዩ ቦታዎች የተከፈቱ የምክር አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ቢኖሩም፤በሚዲያም በነጻ ምክር የሚሠጡ ፕሮግራሞች ቢተላለፉም የሕዝቡ ቀዳሚ ምርጫ ግን አሁንም የሃይማኖት አባቶቹ ካህናት ናቸው፡፡ምክንያቱም፡-

ሀ. የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብና በችግር ወቅት ጠባዩን እንዳይቀይር እያበረታቱ፤በጦርነት በመከራ ጊዜ ወኔው እንዳይከዳው  እያጠነከሩ ይዘውት ከኖሩ ካህናት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው፡፡ በሥጋ ከወለዱት ወላጆቹ ይልቅ ያከብራቸዋል፡፡ ስለዚህ እነርሱ አጠገብ በመገኘቱ ብቻ የሚሰማው ደኅንነት ሌሎች ባለሞያዎች ጋር አይሰማውም፡፡

      ለ. በኢትዮጵያ ምድር አሁንም ቢሆን ሳይንስ በሃይማኖት ላይ የበላይ ለመሆን ስላልቻለና ሕዝቡ እምነቱን ስላልጣለበት ፡፡

      ሐ. ለምሥጢር ትልቅ ግምት የሚሠጠው ሕዝባችን ካህናቱ ዘንድ ምሥጢሩ እንደሚጠበቅለት እርግጠኛ በመሆኑና፤ ይህንንም ከእግዚአብሔር እንደተሠጠው ዋስትና ስለሚቆጥር፤ ከባለሞያዎቹ ጋር ግን ይህ ልምድ ስለሌለውና በመካከላቸውም የምሥጢሩን ድኅንነት የሚያስጠብቅ ዋስትና አለ ብሎ ስለማያምን

መ.ትልቁና ዋነኛው ሕዝቡችግሩን ለካህናቱ ሲነግር ለእግዚአብሔር እንደነገረ ፍፁም ስለሚያምን፤ለሥነ-ልቦና ባለሞያዎች መንገርን ግን ለአንድ ተራ ሰው ችግራችንን ነግረን ከምንጠብቀው ምላሽ የተለየ ስለማይጠብቅ(ካህናቱ ዘንድ ጸሎት፣ ሱባዔ፣ሥልጣን፣ተዐምራት፣መለኮታዊ ኃይል ወዘተ… አለ ብሎ ማመኑ፤ ሌሎቹ ጋር ግን የተለየ ነገር ስለማይጠብቅ)

ሠ.በሕይወት ልምዱ ብዙዎች ለካህናት ነግረው ችግራቸው እንደተፈታ ምስክርነት ስለሚሰማና በአንፃሩ በሥነ-ልቦና አማካሪዎች ዘንድ ስላለው መረጃ ስለሌለው፡፡

ረ.ሕዝቡ(ምዕመኑ) ካህናት ጋር ለምድራዊ ሕይወት መረጋጋትን ለነፍሱ ደግም ሥርየትን ሽቶ እንደመምጣቱ፤ የሥነ-ልቦና ባሞያዎች ጋር የዚህ ዓይነት አገልግሎት እንደማይገኝ ማወቁ ወዘተ…

ስለዚህ ካህናት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሀዘኑ አፅናኝ፣ የደስታው ባራኪ፣የችግሩ አጋር፣የጭንቀቱ መተንፈሻ፣የነፍሱ ምሥጢረኛ እንደመሆናችን ችግርን የሚረግጥ ጽናት ተስፋ መቁረጥን የሚሰብር ጥርካሬ ከእኛ ይጠበቃል፡፡ድቡሽት ላይ ቆሞ ረግረግ ውስጥ ያለን ማውጣት እንደማይቻል፤ ለችግር በቀላሉ እጅ የምንሠጥ ሆነን ሌሎችን መርዳት አይቻለንም፡፡

4.  መንፈሳዊነት፡- መንፈሳዊነት ስል የተገለጠ የሚሠራ የማስመሰል ያልሆነ ማለት ነው፡፡ ይልቁንም ዛሬ ብዙዎቻችን ለመንፈሳዊነት የምንሠጠው ግምት አናሳ ሆኗል፡፡ከመንፈሳዊነት ይልቅ ዘመናዊነት(በተንሸዋረረ ትርጉም) ማርኮናል፡፡ሕዝቡም የኸው ደዌ ተጋብቶበት የእኔ አባት እኮ ዘመናዊ ናቸው ሲል ይደመጣል፡፡የሚጠቅመን ግን ዘመናዊ ሳይሆን መንፈሳዊ አባት ነው፡፡

ላያችን ቢመስለውም ውስጣችን የሚፈልገው ግን ሌላ ነው፡፡ የድሮው የአበው የአነጋገር ለዛ፣ በጨዋታቸው ያለ ቅኔ፣ በነገራቸው ውስጥ ያለ ምሥጢር፣ ከእርጋታቸው የሚፈስ ግርማ ሞገስ ይናፍቀናል፡፡አብሯቸው የኖረ መስቀላቸው፣ ወዝ የጠገበ ዳዊታቸው፣ ዕጣን ያወደው ቀሚስና ካባቸው፣ ንባብና እንቅልፍ ማጣት ያፈዘዘው ዓይናቸው ብዙ ይነግረን ነበር፡፡

ቀደምት አበው ከሕዝቡ ሳይለዩ ሕዝቡንም ሳይመስሉ ይዘውት ኖሩ፤ዛሬ ሕዝቡን መስለን ከሕዝቡ ተለይተን ይዘነው ጠፋን፡፡ትዝታ ምንኛ ደግ ነው፡፡ቢያንስ ዛሬን በትናንት እንታዘበዋለን፡፡ዛሬ እንመገበው ስናጣ የኋሊት ተመልሰን በትናንት እንጠግባለን፡፡

ይብላኝ ትናንትን ለማያውቅ ትዝታ ለሌለው፤

ድሮ እኮ እንዲህ ነበር ብሎ ማውራት ለማይችለው፡፡

ሐዋርያነት ትናንትን ከዛሬ ዛሬን ከዘላለም ጋር ማገናኘት ማዋሐድነው፤ እንደ ሁለቱ የዓለም ብርሃናት፡፡ ለተረዳው ላወቀበት ለኖረበት ለሞተለት!!!

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ጸጋና በረከታቸው ድል የማይነሣ ጽኑ እምነታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን!አሜን!

ቀሲስ ታምራት ውቤ

ሐምሌ 2005 ዓ.ም

                      መታሰቢያነቱ ፡- በፈቱት ምላስ ለሚሰደቡ ባስተማሯቸው ለሚናቁ ለነ የኔታ፤ ለነበሩ ላሉ ለሚኖሩ ትሁን፡፡

Read more...

የሐምሌ ወር ልምምድ

ጸሎት 

-  የጸሎት ሕይወት መፈተሽ ፣በእምነት ፣በትጋት መጸለይ 
-  ለሌሎች : ለዓለም ፣ለሀገር ፣ለቤተክርስቲያን ፣በሞት ለተለዩን ፣ ክፉ ለሚያደርጉብን መጸለይ መለማመድ 
-  የምንለምነውን ማወቅ 
-  ሳያቁአርጡ  መጸለይን መለማመድ /ከፍተኛ ደረጃ/

 

Read more...
Subscribe to this RSS feed

ጠቃሚ አድራሻዎች

መጻሕፍት ቢያነቧቸው

  • * ​ፍቅር 
  • ፍና ቅዱሳን
  • * የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ 
  • * ዝጎራ