Login
Main menu

ትምህርቶች

ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ክፍል ሦስት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በተለያዩ አህጉር ተበትናችሁ በቃሉ ለመኖር ለምትጋደሉ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ ህሊናን ሁሉ የሚያልፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! በቀደመ ጽሑፋችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኑን ድንቅ በሆነ ጽንሰቱ፣ ልደቱና በልጅነት ወራት አስደናቂ ህይወቱ ተመልክተናል፡፡ በይቀጥላል ጌታችን በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ራሱን በትምርቱና በተዐምራቱ በገለጠበት ወቅት የህንኑ አስረግጧል፡፡ ዮሐ 2፥1-12 ፡- በተገለጠው ተዐምራት ጌታችን ውሃውን ወደ ወይን መቀየሩን እናውቃለን፡፡ የውሃ እና የወይን ባህርይ በውስጣቸውም የሚይዙት ውሁድ(Substance) የተለያየ እንደሆነ የተረዳ ነገር ነው፡፡ ጌታ በዚህ ተዐምራቱ ካልነበረ(ከሌለ) ነገር አንድን ነገር ማምጣት(መፍጠር) የሚችል መሆኑን አሳይቶናል፡፡ ዮሐ 5፥1 ፡- 38ዓመት ልምሾ ሆኖ እንደትኋን…
Read more...

ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ክፍል ሁለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በተለያዩ አህጉር ተበትናችሁ በቃሉ ለመኖር ለምትጋደሉ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ ህሊናን ሁሉ የሚያልፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! ባለፈዉ ትምህርታችን የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አልፋና ዖሜጋ ፊተኛዉና ኃለኛው ከዘላለም እስከ ዘላለም ህያው የሆነ አምላክ መሆኑን በተረዳ ነገር አይተናል' በይቀጥላል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን እውነታ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ እናያለን፡፡ ሁሉን ቻይ :- ማለት እንዳሰበ የሚሠራ እንደፈቀደም የሚያከናዉን& ለሥራው ረዳት አጋዥ አማካሪ የማይሻ& ሁሉን ከባህርይ የሚያከናውን& በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም በታች በሁሉ የሚሠራ& በሁሉ የሚያዝ በሁሉ ላይ የሠለጠነ &ማንም ማን ለምን ይህን ታደርጋለህ ብሎ ሊከለክለዉ…
Read more...

ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በ2005ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ ቅዱስ እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መማር እንጀምራለን፡ ትምህርቱ የሚዳስሳቸዉ ነጥቦች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ · ቀዳማዊ ወድኅራዊ ሕያዉ ዘላለማዊ አምላክ ስለመሆኑ · ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት ስለመወለዱ(ስለ ሁለቱ ልደታት) · ስለ ድንቅ ልደቱና የልጅነት ህይወቱ፣ ስለጥምቀቱ፣ ስለትምህርቱና፣ ስለተዓምራቱ፣ ስለህማሙ፣ስቅለቱ፣ ሞቱ፣ትንሣኤዉና ዕርገቱ፣ዳግመኛም ለፍርድ ስለመምጣቱ፣ ወዘተ…ይሆናል፡፡ በቅድሚያ አንድን አካል "አምላክ" ነው ለማለት የአምላክነት ባህርያት ምን እንደሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የሁሉ ነገር የማንነቱ መገለጫ ወሰን ባህርዩ ነውና፡፡ ሰለዚህ የአምላክነት ባህርያት የሚባሉትና የየትኛዉንም ሃይማኖት ተከታይ ወይም ፍልስፍና…
Read more...

...በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ብፁዕ ነው፡፡ መዝ ፩፡፩

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በክፉዎች ምክር ያልሄደ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ብፁዕ ነው፡፡ መዝ ፩፡፩ በመዝሙረ ዳዊት የተመሰገኑ ጠባይዓትንና አካሄዶችን አመለካከቶችንና ተግባራትን “ብፁዕ” በሚል የውዳሴ ቃል እያጀበ ተቀኝቶ እናገኛለን፡፡ ብፁዕ የሚለው ቃል “በፅዐ” ከሚለው የግዕዝ ግሥ የሚወጣ ሲሆን የተደነቀ የተመሰገነ ንዑድ ክቡር የሚለውን ትርጉም ይይዛል፡፡ ከላይ በተቀመጠው ጥቅስ ክቡር ዳዊት ሦስት አንድን ሰው ወደ ጥፋት የሚወስዱ ጉዳዩችን አንስቶ ከእነርሱ በተቃራኒ የሚገኝ ቢኖር ንዑድ ክቡር ነው ይለናል፡፡ ቀዳሚው በክፉዎች ምክር ያልሄደ ብፁዕ(ምስጉን) ነው ይላል፡፡ ምክር አንድን ሰው ክፉውን ጠባይዕ እንዲተው መልካሙን ደግሞ እንዲያፀና አስነዋሪ ተግባር የበጀ መስሎት የሚኖር ካለ እንዲመለስ፤ የተወደደ ሥራ ለመሥራት መንገድ የጠፋውንም…
Read more...

ስቅለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በአብ ስም አምኜ አብን ወላዲ ብዬ በወልድ ስም አምኜ ወልድን ተወላዲ ብዬ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን ሠራፂ ብዬ ምንም ለአጠይቆ አካላት ሦስት ብል በባህርይ በህልውና በፈቃድ በሥልጣን አንድ አምላክ ብዬ በማመን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ እጀምራለሁ፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ ሳያደርጉ እማር አስተምር እጽፍ እደጉስ ቢሉ አይቻልምና፡፡ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት አደረሳችሁ! አባት ሆይ የሚሠሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ታላቅ ቃል የተናገረው በመስቀል ላይ በነበረበት ሰዓት ነው፡፡ ምንም እንኳ በነቢዩ በኢሳይያስ እለተ ዓርብን አስመልክቶ በተናገረው ትንቢት " በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ…
Read more...

ሆሣዕና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሆሣዕና፡- በዚህ ዕለት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ቀን እናስባለን፡፡ በዓለ ሆሣዕና ከጌታችን ፱ቱ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ከሌሊት ጀምሮ በታላቅ መንፈሣዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በሌሊቱና በዑደቱ ሥርዓት ላይ ብቻ ከዘጠኝ ያላነሱ ምስባኮች ስለሚደርሱ ሁሉን መተርጐምን ለጊዜው ታግሠን የትኞቹ እንደሆኑ እንድናውቅ ብቻ ማመላከቻ እንሰጣለን፡፡ ምስባክ፡-መዝ፹፥፫፤መዝ፻፲፯፥፳፮፤መዝ፻፳፩፥፩፤መዝ፻፵፯፥፩፤መዝ፻፲፯፥፳፯፤መዝ፱፥፲፩፤መዝ ፰፥፪፤መዝ፵፱፥፩፤መዝ፷፯፥፴፬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ አራቱም ወንጌላውያን ተባብረው ጽፈውታል፡፡ በማቴ 21፥1-17፤በማር11፥1-10፤ሉቃ19፥29-38፤በዮሐ12፥12-19 በመሆኑም አንዱ ወንጌላዊ የመዘገበውን ብቻ የጽሑፋችን መነሻ ከማድረግ ይልቅ ሁሉንም ወንጌላት መዳሰስን መርጠናል፡፡ ጌታችን ራሱን ለዓለም ገልጦ ማስተማር ከጀመረ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይኽ ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡ በዚሁም…
Read more...

ኒቆዲሞስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ኒቆዲሞስ፡- ጌታችን ኒቆዲሞስ ከሚባል የአይሁድ መምህር ጋር የነበረውን ቆይታ የምናስብበት ሰንበት ነው፡፡ ምስባክ፡- ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው፡፡ ትርጉም፡- ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ ፈተንኸኝ ዓመፃም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡ - ክቡር ዳዊት ከንጉሡ ሳዖል ጋር በነበረው ጠብ የተናገረው ነው፡፡ ምንም እንኳ ሳዖል ቢከፋብኝም ካንዴም ሁለቴ በእጄ ጥለኽው ፈተንኸኝ፡፡ እኔ ግን እንደሆነብኝ ልሁንበት እንዳደረገብኝ ላድርግበት የሚል ክፋትን፣ ቂም፣ በቀልን በልቤ አላገኘኸብኝም፡፡ በአፌም እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሣም ከማለት በቀር ጠላትህን በእጅህ ጥሎልሃል ከሚሉ ጋር ተባብሬ አልተገኘሁም ሲል ነው፡፡ ዳዊት ምን ያህል የዋህና…
Read more...

ገብር ሔር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ገብር ሔር፡- ይህች ዕለት ከልዑል እግዚአብሔር የተለያያ ጸጋን(ሥጦታን) የተቀበልን ሁሉ አንደየሥራችን ምንሞገስባት አልያም የምንወቀስባት ዕለት ናት፡፡ ሁለቱም ለጥቅማችን እንጂ ለጥፋታችን አይደለም፡፡ ምስባክ፡- ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጻድቀከ በማኅበር ዐቢይ፤ መዝ ፴፱፡፰ ትርጉም፡- አምላኬ ሆይ ፈቃድህን እገልጥ(አደርግ) ዘንድ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፤ በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ፡፡ - አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ቃል ከግብር አስማምቼ እገልጣት ዘንድ ወደድሁ፡፡ እንዲህ የተዋቡ ቃላትና ሀሳቦች ሊፈልቁ የሚችሉት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ህብረት ካደረጉ ልቦች(አልባብ)ብቻ ነው፡፡ከሁሉ አስቀድሞ የጌታ እግዚአብሔር ፍቃዱ ምን እንደሆነ አውቃ ትገዛለት ዘንድ ነፍስ በትህትና ወደ ቃሉ ማዕድ መቅረብ ያስፈልጋታል፡፡ ጌታም በመጽሐፍ…
Read more...

ዐቢይ ፆም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በተለያዩ አህጉር ተበትናችሁ በቃሉ ለመኖር ለምትጋደሉ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ ህሊናን ሁሉ የሚያልፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! እስከ ቅርቡ ጽሑፍ አነሣው የነበረውን አሳብ ተግ አድርጌ፤አዲስ የምጽፈውንም ሚያዝያ እስኪብት አቆይቼ በያዝነው የፆም ጉዳይ ላይ ልጽፍላችሁ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከተደነገጉት ዓበይት አፅዋማት አንዱ ፆመ ኢየሱስ (ዐቢይ ፆም ወይም ሁዳዴ) አንዱ ነው፡፡ ጌታ ስለፆመው ፆመ ኢየሱስ ወይም ዐብይ ፆም፤ ሁሉ ተስተካክሎ ስለሚፆመውም “ሁዳዴ” ተብሏል፡፡ የሁዳድ እርሻን ሁሉ በህብረት እንዲሰራው በዚሁ አንፃር ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እፀድቅ አይል ጻድቅ፣ እቀደስ አይል ቅዱስ፣እነፃ አይል ንፁህ፣ ኃይል መንፈሳዊ አገኝ አይል ኃይል የባህርዩ የሆነ፣ ከኃጢአት…
Read more...
Subscribe to this RSS feed

ጠቃሚ አድራሻዎች

መጻሕፍት ቢያነቧቸው

  • * ​ፍቅር 
  • ፍና ቅዱሳን
  • * የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ 
  • * ዝጎራ