በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በተለያየ አህጉር አንድ ጊዜ ስለተሠጠች የቅዱሳን ሃይማኖት እየተጋደላችሁ፤ ዲያብሎስንና ሥራውን ሁሉ በእምነት ኃይል እየተቃወማችሁ የጌታችንን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም መምጣት በተስፋ ለምትጠባበቁ የመንፈስ ልጆቼ የተላከ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! ባለፉት ጊዜያቶች በላክሁላችሁ ጦማሮች ቅዱስ እግዚአብሔርን በመከተልና፤በቅድስና ስፍራው በቤቱ በመገኘት የምናገኘውን መልካም ነገርና፤ ምርጫችንም ምን መሆን እንዳለበት ተነጋግረናል፡፡ ለዛሬ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን ሌላ ሦስተኛ ጠቃሚ ነጥብ አናያለን፡፡ ከብዙ ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ(ቃል) ይሻለኛል መዝ118፥70 ነብዩ ዳዊት በዚህ የመዝሙር ቃሉ ሁለት በሰው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡ (የሚወደዱ) እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አነፃጽሯል፡፡ አንዱ ጊዜያዊ ሌላው ዘላለማዊ፣…
Read more...